ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም 45 ሚሊዮን ዜጎች የረሀብ አደጋ እንዳዣበበባቸው ተመድ ገለጸ
በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር በ3 ሚሊዮን ጨምሯል
ጦርነት፣ኮቪድ እና የአየር ንብረት ለውጥ የረሀብ ምክንያቶች ናቸው
ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለማችን 45 ሚሊዮን ዜጎች የረሀብ አደጋ እንዳዣበበባቸው ተመድ ገለጸ፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባወጣው ሪፖርት በዓለማችን 45 ሚሊዮን ዜጎች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ለረሃብ አደጋ የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር 42 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ቁጥሩ ወደ 45 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ድርጅቱ አክሏል፡፡
ጦርነት፣የኮሮና ቫይረስ ጉዳት እና የአየር ንብረት መለዋወጥ ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር ለመጨመሩ ምክንያቶች መሆናቸውንም የድርጅቱ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
የረሃብ አደጋ ካንዣበባቸው አገራት መካከልም የመን፣ሶሪያ፣አፍጋኒስታን፣ ኢትዮጵያ ፣አንጎላ ፣ሶማሊያ ፣ኬንያ፣ሀይቲ እና ቡሩንዲ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ድርጅቱ እነዚህ ዜጎችን ከተጋረጠባቸው የረሃብ አደጋ ለመከላከልም 7 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ እንዳሉት አሁን ላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም 23 ሚሊዮን ዜጎችን ለእለት የሚያስፈልግ ምግብ በማድረስ ላይ መሆኑን ተናግረው አገራት እና ተቋማት ተ,ማሪ ድጋፎችን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
የነዳጅ እና የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በየጊዜው እየጨመረ መሆኑ ለምግብ ዋስትና ሌላኛው ፈተና ሆኗል የሚሉት ዳይሬክተሩ ግጭቶችን በማስቆም እና ሌሎች ድጋፎችን ሀገራት እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡