ማዳጋስካር በከሸፈው የፕሬዚዳንት ግድያ ላይ የተጠረጠሩ 5 ጀነራሎችን አሰረች
ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊናን ለመግደል ታስቦ የነበረው እቅድ ባሳለፍነው ሳምንት ከሽፏል መባሉ ይታወሳል
በዚህ የፕሬዚዳንቱ ግድያ እቅድ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 5 ከፍተኛ የጦር ጀነራሎችን ጨምሮ 21 ሰዎች ታስረዋል
ማዳጋስካር በከሸፈው የፕሬዚዳንት ግድያ ላይ የተጠረጠሩ 5 የጦር ጀነራሎችን አሰረች።
ከአንድ ሳምንት በፊት የአገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት የማዳጋስካር ፕሬዘዳንት አንድሪ ራጆሊናን ለመግደል ታስቦ የነበረውን እቅድ ማክሸፉን ገልጸ ነበር።
በዚህ የግድያ እቅድ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 5 ከፍተኛ የጦር ጀነራሎችን ጨምሪ 21 ካፒቴኖች፤ፖሊሶች እና ሌሎች ተሳታፊ ግለሰቦች መያዛቸውን ተገልጿል።
የዚህን የግድያ እቅድ እየመረመረው ያለው የምርመራ ቡድን ከ250 ሺህ በላይ ዶላር እንዳይንቀሳቀስ ማገዱንም ገልጿል።
እንደ አገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለጻ የውጭ ዜጎች ሳይቀር ተሳትፈውበታል የተባለውን የፕሬዘዳነት አንድሪ ራጆሊና የግድያ እቅድ ባይሳካም ምርመራው አሁነም እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
በዚህ ግድያ ላይ አሁን በአገሪቱ ብሔራዊ ጦር እና በጡረታ ላይ የነበሩ ወታደራዊ አመራሮች እና የውጭ የአገር ዜጎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
የግድያ እቅዱ አላማው ፕሬዚዳንቱን ከመግደል ጀምሮ ሌሎች የማዳጋስካር የፖለቲካ አመራሮችን በማስወገድ የፖለቲካ ችግሮችን መፍጠር መሆኑን ፍራንስ 24 ባሳለፍነው ሳምንት ዘግቧል።
ማዳጋስካር ከአንድ ወር በፊት የነጻነት በዓሏን ባከበረችበት ወቅት የፕሬዘዳንት አንድሪ የቀኝ እጅ በመባል የሚታወቁት ጀነራል ሪቻርድ ራቫሎማናን የመግደል ተሞክሮ እንደከሸፈ ዘገባው በተውስታ ጠቁሟል።
የአሁኑ የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ከሁለት ዓመት በፊት ነበር በምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት።
የ44 ዓመቱ ፕሬዚዳንት አንድሪ በፈረንጆቹ 2009 በአገሪቱ ወታደር ታግዚው እስከ ፈረንጆቹ 2014 ድረስ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለውም ነበር።
27 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ደቡበ አፍሪካዊቷ አገር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በፈረንጆቹ 1960 ዓመት ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የቀድሞዋ ማላጋሲ ሪፐብሊክ ስሟን ወደ አሁኑ ማዳጋስካር ቀይራለች።