በሩሲያ በኩል ያሉ የኑክሌር ማስፈራሪያዎች ለምዕራባውያን "የመጨረሻ ጥሪ" ናቸው ተባለ
ኮሎኔሉ በሩሲያ እና በኔቶ መካከል ሊኖር የሚችል ጦርነት ወደ ኑክሌር ጦርነት እንደሚያመራ ተናግረዋል
ለክሬሚሊን ቅርብ የሆኑ ወታደራዊ አዛዦች እና የሚዲያ ሰዎች በተደጋጋሚ ማስፈራሪያ አሰምተዋል
በሩሲያ በኩል ያሉ የኑክሌር ማስፈራሪያዎች ለአሜሪካ እና አውሮፖውያን "የመጨረሻ ጥሪ" ናቸው ተባለ።
ሩሲያ ዩክሬንን በሚያግዙ ምዕራባውያን ላይ የኑክሌር መሳሪያ ልትጠቀም ትችላለች የሚል ስጋት ተፈጥሯል።
ለክሬሚሊን ቅርብ የሆኑ ወታደራዊ አዛዦች እና የሚዲያ ሰዎች በተደጋጋሚ ማስፈራሪያ አሰምተዋል።
የአሜሪካው ጋዜጣ ኒውስዊክ በሩሲያ በኩል የሚደመጡት ማስፈራሪያዎች ለአሜሪካ እና አውሮፖውያን "የመጨረሻ ጥሪ ናቸው" ሲል ገልጿቸዋል።
ኒውስዊክ የሩሲያ ብሮድካስተር የሆነው ቭላድሚር ሶልቪዮቭ ከሩሲያ ጋር ያለው ጦርነት የሚባባስ ከሆነ የኔቶ ሀገራትን እናጠፋለን ማለቱን ዘግቧል።
እንደጋዜጣው ከሆነ የሶሎቪቭ መግለጫ ሩሲያ ከኔቶ ጋር ወደ ግጭት የምትገባ ከሆነ የሩሲያ ግዛት የሆነችው ካሊንግራድ ትከበባለች ላሉት የኔቶ ኮማንደር መልስ ነው።
ካሊንግራል ከዋናዋ ሩሲያ የተነጠለች፣ በሉታንያ እና ፖላንድ የተከበበች በባልቲክ ባህር ያለች የሩሲያ ዋነኛ ወደብ ነች።
የሩሲያ ብሮድካስተር ማስፈራሪያ ብቸኛው አይደለም። ብሮድካስተሩ አስተያየት የሰጠው ጡረታ የወጡት ኮሎኔል ሚካኤል ኮዳሪዮንኮ በባልቲክ ባህር አቅራቢያ ባሉት የኔቶ አባላት ላይ ተመሳሳይ ማስፈራሪያ ከሰጡ በኋላ ነው።
ኮሎኔሉ በሩሲያ እና በኔቶ መካከል ሊኖር የሚችል ጦርነት ወደ ኑክሌር ጦርነት እንደሚያመራ ተናግረዋል።
ሩሲያ በተለይም በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ከኔቶ ጋር ያላት መፋጠጥ ጨምሯል።