ኢራን ከመቼው ጊዜ በላይ ችግር መደቀኗን የአለምአቀፉ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ሃላፊ ተናገሩ
ኢራን ኑክሌር ማበልጸጊያ ማእከሎችን እያስፋፋች መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል
ኃላፊው የወቅቱ ችግር ከሆነው የየክሬን ጦርነት ይልቅ በኢራን ያለው የኑክሌር ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል
ኢራን ከመቼውም ጊዜ በላይ ችግር መደቀኗን የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ጠባቂ ኃላፊ ራፋኤል ግሮስ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው ይህን ያሉት ኢራን ኑክሌር ለማበልጸግ እየተጠቀመችበት ያለውን የላቁ ሴንትሪፉጅ ቁጥር በማጣቀስ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በቅርብ ጊዜ ባወጣወ ሚስጥራዊ ሪፖርቶች ኢራን በናታንዝ እና ፎርዶው በሚገኙ የከርሰ ምድር ማበልፀጊያ ፋብሪካዎቿ ላይ የላቁ ሴንትሪፉሶችን በብዙ ክላስተሮች ወይም ስብስቦች እየከለለች እና እያበለፀገች ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በ2015 ከኢራን ጋር የተፈራረመውን የኒውክሌር ስምምነት ለማደስ ከአሜሪካ ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ቆሟል። ኢራን አለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በልተፈቀደ ቦታ የሚያደርገውን የዩራኒየም ምርመራ እንዲያቆም መጠየቋ ከአሜሪካ ጋር ያላግባባት ጉዳይ ሆኗል፡፡
በአሜሪካ በተደረገ ውይይት ግሮሲ የወቅቱ ችግር ከሆነው የየክሬን ጦርነት ይልቅ በኢራን ያለው የኑክሌር ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡
ግሮሲ ለካርኔጊ አለም አቀፍ የኑክሌር ፖሊሲ ኮንፈረንስ "ይህ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ነው፤ ገለልተኛ የሆነ ቃል እመርጣለሁ ። እሱ በየቀኑ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ችግር ነው" ብለዋል፡፡