ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ በሶስት ሰዎች ላይ የእስር ማዘዣ ትዕዛዝ አውጥቷል
ፍርድ ቤት ትዕዛዙን ያስተላለፈው በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው
ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው።
ከ13 ወራት በፊት ለፍልስጤም ነጻነት እንደሚታገል የገለጸው ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡
እስራኤል ይህን ጦርነት የምታቆመው ሁሉንም ታጋቾች እስከምታስለቅቅ እና ሐማስ ዳግም ለእስራኤል ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ከተመታ በኋላ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡
በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ምክንያት ከፍልስጤም በኩል ከተገደሉት ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች ውስጥ 80 በመቶዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ተብሏል።
እንዲሁም በእስራኤል በኩል ደግሞ 1 ሺህ 200 ንጹሃን መገደላቸውን ተመድ በሪፖርቱ ላይ ገልጿል።
መቀመጫውን ጀኔቭ ስዊዘርላንድ ያደረገው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በሁለቱም አመራሮች ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።
የእስር ማዘዣው በጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ መከላከያ ሚንስትር ዮአቭ ጋላንት እና በሐማስ ኮማንደር መሀመድ አልማስሪ ላይ ወጥቷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
እስራኤል ከዚህ በፊት የአይሲሲን የእስር ማዘዣ ሊያወጣ እንደሚችል በተገለጸበት ወቅት ጉዳዩን ተቃውማ ነበር።