የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ኔታንያሁን በማሰር አሳልፎ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ 120 አባል ሀገራት ያሉት ሲሆን፤ 33ቱ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው
አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና በቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።
አይሲሲ ኔታንያሁ እና ጋላንት በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው የእስር ማዘዣ ያወጣባቸው።
ፍርድቤቱ የጥቅምት 7ቱን የሃማስ ጥቃት አቀነባብሯል የተባለው የቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ አልቃሳም ብርጌድ መሪ መሀመድ ዴይፍ ላይም የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ይፋ አድርጓል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ 124 የአለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት አባል ሀገራት መጓዝ የመታሰር አደጋ ደቅኖባቸዋል።
የፍርድቤቱ አባል ሀገራት የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ሰዎችን አሳልፈው ለመስጠት ስለተስማሙ ኔታንያሁ እና ጋላንት ወደ 124ቱ ሀገራት መጓዝን ላይደፍሩ ይችላሉ ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታያሁ በማሰር አሳልፎ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነትን የፈረሙ የዓለም ሀገራት 124 ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ውስጥ 33 ሀገራት ከአፍሪካ መሆናቸው አሃዞች ያመለክታሉ።
በዚህ መሰረት ከአፍሪካ ሴኔጋል፣ ጋና፣ ማሊ፣ ሌሴቶ፣ ቦትስዋና፣ ሴራሊዮን፣ ጋቦን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሴንተራል አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቤኒን፣ ሞሪሺየስ፣ ኒጀር፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ፣ ናሚቢያ እና ጋሚቢያ።
እንዲሁም ታንዛኒያ፣ ማላዊ፣ ጂቡቲ፣ ዛምቢያ፣ ጊኒ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ኮንጎ፣ ላይቤሪያ፣ ኬንያ፣ ኮሞሮስ፣ ቻድ፣ ማዳካስካር፣ ሲሸልስ፣ ቱኒዚያ፣ ክፕቭርዴ እና ኮትዲቯር ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታያሁን ጨምሮ እስር የወጣባቸውን ሰዎች አሳልፎ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
ከአውሮፓም 42 ሀገራት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታያሁን ጨምሮ እስር የወጣባቸውን ሰዎች አሳልፎ የመስጠት ግዴታ አለባቸው የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ቤልጂየም፣ ፈረንሳይ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ብሪታኒያ፣ አይርላንድ፣ ጣሊያን፣ ስዊድን፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ እና ሌሎችም ሀገራት ተጠቃሽ ናቸው።
ከእሲያ ፓስኪክ ሀገራት መካከል ደግሞ አውስትራሊያሰ፣ ባንግላዴሽ፣ ጃፓን፣ ኒውዚላድ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ፍሊስጤም እና ሌሎችም ይገኙበታል።
በተጨማሪም ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ካናዳ፣ ምኪሶኮ፣ ፔሩ እና ፓራጉዋይን ጨምሮ ሌሎችን የሰሜን እና የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታያሁን ጨምሮ እስር የወጣባቸውን ሰዎች አሳልፎ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ አሜሪካ ለማቅናትም በፍርድቤቱ አባል ሀገራት ማረፍ (ትራንዚት ማድረግ) አይችሉም።
እስራኤል አጋሯ አሜሪካን ጨምሮ እንደ ቻይና፣ ሩሲያ እና ህንድ ያሉ ሀገራት የፍርድ ቤቱን መመስረቻ እስካሁን ካለመፈረማቸው ጋር ተያየዝ በቁጥጥር ስር የማዋል ግዴታ የለባቸውም።