አይሲሲ የእስራኤል ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን ገለጸ
ፍርድ ቤቱ እስራኤል አለምአቀፍ የጦር ህጎችን እንድታከብርም ጠይቋል
ካን ሰፋሪዎች በዌስትባንክ የሚያደርጉት ጥቃት ተቀባይነት የሌለው እና ዝም ተብሎ የማይታለፍ ነው ብለዋል
አይሲሲ የእስራኤል ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን ገለጸ
አለምአቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት(አይሲሲ) በዌስትባንክ የእስራኤል ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፍርድ ቤቱ እስራኤል አለምአቀፍ የጦር ህጎችን እንድታከብርም ጠይቋል።
"በጋዛ ዶክተሮች ያለመብራት ቀዶ ጥገና የሚያደርጉበት ምንም ምክንያት የለም" ሲሉ የአይሲሲ አቃቤህግ ካሪም ካን እስራልን እና የፍልስጤም ኦቶሪቲ የሚያስተዳድራትን ዌስትባንክን ከጎበኙ በኋላ ተናግረዋል።
አቃቤ ህጉ እስራኤል ህግን ማክበር አለባት፣ አሁን ካላከበረች በኋላ ቅሬታ ማቅረብ የለባትም ብለዋል።
ሀማሳን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ወጥና እየንቀሳቀሰች ያለችው እስራኤል የጋዛ ነዋሪዎች አካባቢዎችን እንዲለቁ በማድረግ ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላበታለች።
በኢራን የሚደገፈው ሀማስም በእራኤል ላይ ጥቃት እየሰነዘረ ነው።
ካን ከእስራኤል በተጨማሪ ሀማስ የጦርነት ህግን እንዲያከብር እና በተከበበችው ጋዛ ውስጥ የሚደርሱ እርዳታዎችን እንዳያባክን ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር በሀማስ የተፈጸመው ድርጊት ከባድ የሚባል አለምአቀፍ ወንጀል መሆኑን የገለጹት ካን ፍርድ ቤቱ እስራኤል የምታደርገውን ምርመራ ለማገዝ ዝግጁ ነው ብለዋል።
ካን አክለው እንደተናገሩት ሰፋሪዎች በዌስትባንክ የሚያደርጉት ጥቃት ተቀባይነት የሌለው እና ዝም ተብሎ የማይታለፍ ነው።
በጋዛ በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው ተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱን ተከትሎ 800 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል