ከቅዳሜ ወዲህ በጋዛ ከ800 በላይ ፍሊስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ
ቅዳሜ እለት ብቻ በ24 ሰዓታት ውስጥ በእስራኤል አየር ድብደባ 700 ፍሊስጤማውያን ሞተዋል
እስራኤል ከፍተኛ የሃማሰ አዛዥ ገደልኩ ስትል፤ ሃማስ 3 የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉ ተነግሯል
ከተኩስ አቁም በኋላ ዳግም ያገረሸው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት አሁን ላይ ተባበሶ መቀጠሉ ተነግሯል።
እስራኤል በጋዛ የምተካሂደውን የአየር ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ የእስራኤል ጦር በጋዛ እያካሄደ የሚገኘውን የምድር ዘመቻ አስፋፈቶ መቀጠሉ ተነግሯል።
እየተባባሰ በመጣው ጦርንት ከቅዳሜ ወዲህ ብቻ ከ800 በላይ ፍሊስጤማውያን በእስራኤል የአየር ድብደባ መገደላቸውን የፍሊስጤም ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ700 በላይ ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል የተባለ ሲሆን፤ ይህም ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በአንድ ቀን ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ነው።
እስራኤል የጃባሊያ የስደተኞች ካምፕን ኢላማ በማድረግ ድብደባ ፈጽማለች የተባለ ሲሆን፤ በርካታ ቤቶች መፈራረሳቸው እና አሁንም ሰዎች በፍርስራሽ ስር ተቀብረው እንደሚገኙም ተነግሯል።
ተናንት ቀን እና አዳሩን የእስራኤል የአየር ድብደባ የቀጠለ ሲሆን፤ በዚህም ከ100 በላይ ፍሊስጤማወያን መገደላቸውም ነው የተገለፀው።
በሰሜን ጋዛ ከሃንዩኒስ የሚገኙ ፍሊስጤማውያን መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ከእስራኤል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸውም ተነግሯል።
እስራኤል በጥቅምት 7 የሃማስ ጥቃት ላይ ተሳትፎ የነበረውን እና ሃይታም ኩዋራጂ የተባለ የሃማስ ኮምንደር መግደሏን አስታውቃለች።
በጋዛ በጦርነቱ ላይ የነበሩ 3 የእስራኤል ወታደሮችም በሃማስ መገደላቸውን እስራኤል አስታውቃለች።
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ አሁን ላይ ወደ ሁለተኛ ወሩ እየቃረበ ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ጊዜም ከ15 ህ 500 በላይ ፍሊስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን፤ ከ41 ሸህ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።