እስራኤል ደቡብ ጋዛን እየደበደበች ነው፤ አሜሪካ እንዲቆም እየጠየቀች ነው
የሀማስ ምክትል ኃላፊ እስራኤል ተኩስ ካላቆመች እና ያሰረቻቸውን ፍልስጤማውያን ከእስር ካልፈታች ታጋቾች እንደማይለቀቁ አሳውቋል
ተመድን ጨምሮ በርካታ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት በጋዛ ተኩስ ቆሞ፣ ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ እና ተጋቾች እንዲለቀቁ ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው
እስራኤል ደቡብ ጋዛን እየደበደበች ነው፤ አሜሪካ እንዲቆም እየጠየቀች ነው።
በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው እና ሁለት ጊዜ የተራዘመው ተኩስ አቁም ከተጣሰ በኋላ እስራኤል ደቡባዊ ጋዛን እየደበደች ትገኛለች።
አሜሪካ፣ እስራኤል እያደረሰች ያለውን ድብደባ እንድታቆም እየጠየቀች ነው።
የሀማስ ምክትል ኃላፊ እስራኤል ተኩስ ካላቆመች እና ያሰረቻቸውን ፍልስጤማውያን ከእስር ካልፈታች ታጋቾች እንደማይለቀቁ አሳውቋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት ሀማስ 17 የእስራኤል ታጋቾችን ለመልቀቅ ገብቶ የነበረውን ቃል አፍርሷል ብለዋል።
በእስራኤል እና በሀማስ መካከል ያለው የቅርብ ጊዜ ግጭት የተቀሰቀሰው ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር ድንበር በመጣስ በእስራኤላውያን ላይ ግድያ እና እገታ መፈጸሙን ተከትሎ ነበር።
እስራኤል በአሁኑ ወቅት በደቡባዊ ጋዛ ካን ዮኒስ መጠነሰ ሰፋ ጥቃት እየወሰደች ነው ተብሏል።
በዚህ ጥቃት 200 ገደማ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለስሌጣናት ተናግረዋል።
እስራኤል ሀማስን ከሚደግፈው የሊባኖሱ ሂዝቦላ ጋር በሰሜን ድንበሯ በኩል የተኩስ ልውውጥ እያደረገች ትገኛለች።
ተመድን ጨምሮ በርካታ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት በጋዛ ተኩስ ቆሞ፣ ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ እና ተጋቾች እንዲለቀቁ ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው።