የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ጥያቄ ቀረበ
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል እና ሐማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል
የእስር ማዘዣው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እና የሐማስ ጦር አዛዦችንም ይመለከታል
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው የአለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) አቃቤ ህግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ሀማስ ከሳባት ወር በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
ይህን ተከትሎ እስራኤል በሀማስ ስም በንጹሀን ዜጎች ላይ ጥቃት ከፍታለች የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ ሀገራት እና ሰብዓዊ ተቋማት በመሰንዘር ላይ ናቸው።
እስራኤል ሀማስ ላደረሰው ጥቃት እየሰጠችው ባለው ራስን መከላከል ዘመቻ ከ35 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላዊያን ተገድለዋል።
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በዚህ የንጹሃን ዜጎች ግድያ ተጠያቂ ናቸው ባላቸው መሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አስተላልፏል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮቭ ጋላንት ከእስራኤል በኩል ከሐማስ በኩል ደግሞ ሶስት አመራሮች የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ቀርቧል።
እስራኤል በሀማስ ላይ "ሙሉ ድል" ትቀዳጃለች ብለው እንደማያምኑ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናገሩ
በጋዛ የሃማስ የፖለቲካ ክንፍ ሃላፊው ያህያ ሲንዋር፣ የሐማስ ጦር አዛዥ መሀመድ አል ማስሪ እንዲሁም በዶሃ የሚገኙት የቡድኑ የፖለቲካ መሪው ኢስማኤል ሀኒያህ ናቸው በፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው፡፡
ደቡብ አፍሪካ፣ ቱርክ እና ሌሎችም ሀገራት እስራኤል ንጹሀንን በመግደል እና ሌሎች የከፋ ጥቃት አድርሳለች በሚል በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት እንድትጠየቅ ግፊቶች ሲያደርጉ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡
እስራኤልም ሆነች ሐማስ የጦር ወንጀሎችን እንዳልፈጸሙ ተናግረው በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ያወጣውን የእስር ማዘዣ ውድቅ አድርገዋል፡፡