የጦር ወንጀሎችን የሚመረምረው አለምአቀፍ ፍ/ቤት ሲስተሙ መጠለፉን ገለጸ
ፍ/ቤቱ በፈረንጆቹ በ2002 በኔዘርላንድ ሃጉ ከተማ የተቋቋመ የጦር ወንጀሎቾን እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚዳኝ ቋሚ ችሎት ነው

ፍ/ቤቱ ባወጣው አጭር መግለጫ"ለዚህ የሳይበር ሴኩሪቱ አደጋ አስቸኳይ ምላሻ ተጠስቷል" ብሏል
የጦር ወንጀሎችን የሚመረምረው አለም አቀፉ የወንጀለኞቾ ፍርድ ቤት(አይሲሲ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኮምፒተር ኔቶርኩ ላይ ያልተለመደ እንቅስቃሴ አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።
ጠለፋው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እና ችግሩ ስለመፈታቱ ወይም ስለአለመፈታቱ የተጠየቁት የፍ/ቤቱ ቃል አቀባይ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፍ/ቤቱ ባወጣው አጭር መግለጫ"ለዚህ የሳይበር ሴኩሪቱ አደጋ አስቸኳይ ምላሻ ተጠስቷል" ብሏል።
ፍ/ቤቱ በፈረንጆቹ በ2002 በኔዘርላንድ ሃጉ ከተማ የተቋቋመ የጦር ወንጀሎቾን እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚዳኝ ቋሚ ችሎት ነው።
በአሁኑ ወቅት የፍ/ቤቱ አቃቤ ህጎች በዩክሬን፣በኡጋንዳ፣ በቬንዙዌላ፣ በአፍጋኒስታን እና በሌሎች ሀገራት 17 ምርመራዎችን እያካሄዱ ይገኛሉ።
ይህ ፍ/ቤት ባለፈው መጋቢት ወር ህጻናትን ህገወጥ በሆነ መንገድ ከዩክሬን አስወጥተዋል በሚል በሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ላይ ያወጣው የእስር ትዕዛዝ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ክሬሚሊን የፍ/ቤቱን ክስ ወድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
የትኛው የሲስተሙ ክፍል መጠለፉን ፍ/ቤቱ ይፋ ባያደርግም ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ምስክሮች ስም እና የወንጀልን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሹ ሚስጥራዊ ሰነዶች የሚባሉ ናቸው።