አሜሪካ አይሲሲ እስራኤል በፍሊስጤም ግዛቶች ፈጽማዋለች ስላለው የጦር ወንጅል ላይ የሚያደርገውን ምርመራ እንደምትቃወም አስታውቃለች
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዘዳንት ካማላ ሀሪስ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ አሜሪካ አይሲሲ እስራኤል በፍሊስጤም ግዛቶች ፈጽማዋለች ባለው የጦር ወንጅል ላይ የሚያደርገውን ምርመራ እንደምትቃወም አስታውቃለች፡፡
ኃይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንና ሃሪስ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የስልክ ውይይት ነው፡፡ አሜሪካ ይህን ያለችው የአይሲሲ አቃቤ ህግ በእስራኤል ላይ ምርመራ እጀምራለሁ ካሉ ከአንድ ቀን በኃላ ነው፤ የአቃቤ ህጓ ንግግር በዋሽንግተንና በእስራኤል ወዲያውኑ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
በብሪታኒያው አቃቤ ህግ የተተካው አቃቤ ህግ ፋቶ ቤንሶዳ በፈረንጆቹ 2019 በዌስትባንክና ባጋዛ ሰርጥ የጦር ወንጅል መፈጸሙን ገልጸው ነበር፡፡ አቃቤ ህጓ የእስራኤል መከላከያ ኃይሎችና የታጠቁ የሃማስ ሃይሎችን በስም በመጥቀስ ጥፋት ማድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡
ሃሪስና ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ አይሲሲ በእስረኤል ሃይል ላይ የሚደረግን ምርመራ እንደሚቃወሙ መነጋገራቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡ሁለቱ ሀገራት በቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩና በተለይም የኢራንን የኒውክሊየር ፕሮግራምና አደገኛ ያሉትን ጸባይ ላይ እንደሚተባበሩ አስታውቀዋል፡፡
ሀሪስ አሜሪካ ለእስራኤል ጸጥታ ያላትን ያልተቆጠበ ድጋፍ ገልጸዋል፡፡ ባይደን በፈረንጆቹ 2015 በኢራንና አለም ሃያል ሀገራት መካከል የተፈረመውን ስምምት ለመከለስ መሞከራቸው ከኒታያኒያሁ ጋር ሊያጋጫቸው ይችላል ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታኒያሁ የኒውክሊየር ስምምነቱን የሚቃወሙ ሲሆን ፕሬዘዳንት ትራምፕ ስምምነቱን በፈረንጆቹ 2018 በመተዋቸው አድንቀዋቸዋል፡፡ ሃሪስ ከዚህ በተጨማሪም የእስራኤልን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዘመቻ አድንቀዋል፣ በጋራ እንደሚሰሩም መነጋገራቸውንመግልጫው አስታውቋል፡፡