አለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ህይወት አድን እርዳታ ትግራይ ማድረሱን አስታውቀ
ኮሜቴው በአማራ እና አፋር ክልሎችም የሰብአዊ እርዳት ማድረሱን እንደሚቀጥል ገልጿል
እርዳታ የሚያደርሱ ተጨማሪ በረራዎች እንደሚኖሩና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ በመንገድ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያደርስ ኮሚቴው ገልጿል
አለምአቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ ከባለፈው የፈረንጆቹ መስከረም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የህክምና እርዳታ ማድረሱን አስታውቋል፡፡
ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ በባለስልጣናት ድጋፍና አመቻችነት አማካኝነት አስፈላጊ መድሃኒቶችን ጨምሮ በአስቸኳይ የሚፈለጉ ድጋፎች በዛሬው እለት መቀሌ ደርሰዋል፡፡
ትግራይ የደረሱት መድኃኒቶች በክልሉ ውስጥ ባሉ ጤና ጣቢያዎች ይሰራጫሉ ብሏል ኮሚቴው፡፡
በኢትዮጵያ የኮሚቴው ልዑካን የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ "ይህ የመጀመሪያው ጭነት ወደ ሆስፒታሎች መድረሱ ትልቅ እፎይታ ነው”ብለዋል። "ይህ እርዳታ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሕይወት መስመር ነው፣ እና እነዚህ አቅርቦቶች መቀጠላቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በበቂ ሁኔታ ማጉላት አልችልም።"
ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ እርዳታ የሚያደርሱ ተጨማሪ በረራዎች እንደሚኖሩና ሁኔታቆች ሲፈቅዱ በመንገድ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያደርስ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡
ኮሜቴው በአማራ እና አፋር ክልሎችም ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ ይቀጥሏል ብሏል፡፡
ሚስተር ባራሳ አክለውም "በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ይሰራሉ፤ ለህዝቡ አስቸኳይ ፍላጎት ምላሽ ይሰጣሉ፡፡"
ኮሚቴው ሁሉም በግጭቱ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ማመቻቸት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡