ኢትዮጵያ የውሃ ክፍፍል ጉዳይ 11ዱን የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚመለከት ነው አለች
አምባሳደር ዲና የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት እክል ቢገጥመው ሁለቱም ሀገራት ይጎዳሉ ብለዋል
ኢትዮጵያ የራሷን የውሃ ሙሌት ደንብ ማቅረቧን ተከትሎ የተቋረጠው የግድቡ ድርድር በመጭው ሰኞ ይቀጥላል
ኢትዮጵያ የራሷን የውሃ ሙሌት ደንብ ማቅረቧን ተከትሎ የተቋረጠው የግድቡ ድርድር በመጭው ሰኞ ይቀጥላል
ከሰሞኑ ኢትዮጵያ የራሷን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ደንብ ማቅረቧን ተከትሎ ግብጽና ሱዳን በዚህ ሰነድ ላይ ለመወያየት ጊዜ እንደሚፈልጉ በመግለጻቸው ድርድሩ መቋረጡ ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረት ድርድሩ በሚቀጥለው ሰኞ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በግድቡ የድርድር ሂደትና በሌሎች የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ አቅርባዋለች የተባለው “የግድብ ሙሌት ደንብ” ይዘት ምን እንደሆነ ለቀረበው ጥያቄ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሰነዱ የተለየና አዲስ ሳይሆን ቀደም ሲል የነበረ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ አምባሳደሩ እንደተናሩት ሰነድ አሁን ውሃ መሞላት እንዳለበትና ስለ ውሃ ክፍፍል ጉዳይ ግን ሌላ ጊዜ እንወያይ የሚል ነው፡፡
የውሃ ክፍፍል ጉዳዩ የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ተፋሰስ ሀገራት መሆኑን ኢትየጵያ መግለጿን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
የናይል(ጥቁር አባይና ነጭ አባይ) ተፋሰስ ሀገራት 11 በመሆናቸው ሁሉም በክፍፍሉ እንደሚመለከታቸው አምባሳደር ዲና ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት ወደ ውኃ ክፍፍሉ ከኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በተጨማሪም የተፋሰስ ሀገራትን ማለትም ደቡብ ሱዳን፣ሩዋንዳ፣ታንዛኒያ፣ኡጋንዳ፣ቡሩንዲ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ኤርትራና ኬንያንም የሚመለከት በመሆኑ እነርሱም መሳተፍ አለባቸው አሁን ግን የውኃ ሙሌቱን ብቻ ነው መነጋገር ያለብን የሚል ሃሰብ መቅረቡን ተሰምቷል፡፡
ግብጽ በተደጋጋሚ ድርድር ጀምራ ማቋረጧ አሰልች ቢሆንም ጉዳዩ የሉዓላዊት በመሆኑ ሁሌም በድርድር ጥሩ ነገር ይመጣል ብለን በማሰብ እስካሁን ድርድሩ ላይ ቆተናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባቀረበችው የውኃ ሙሌት ደንብ ላይ በቀጣይ ሰኞ ነሀሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ውይይት ይደረጋል ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡ከሰሞኑ አሜሪካ የሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ ኢትዮጵያ ጊዜው ረፍዶባታል ብላለች መባሉን ተከትሎም አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲበላሽ አትፈልግም ነገር ግን ግንኙነቱ እክል ቢገጥመው የምትጎዳው ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አሜሪካም ነች ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፍላጎት አሜሪካ ልክ እንደ አውሮፓ ሕብረትና እንደሌሎች የታዛቢነት ሚናዋን ብቻ ይዛ እንድትቀጥል ብቻ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና ብሔራዊ ጥቅምን በትኛው ጫና ድርድር ውስጥ አናስገባም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከራሷ የውሃ ድርሻ ተጠቅማ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉልህ ተጽእኖ ሳታሳድር ለልማት አለማ ግድብ መገንባቷ ተገቢ መሆኑን በተደጋጋሚ ስገልጽ ቆይታለች፡፡ ሱዳን የግድቡን መገንባት ከመጀመሪያው ጀምሮ እንደማትቃወም ገልጻ፤ነገርግን አስተዳደሩና አሞላሉን በሚመለከት የሶስትዮች ስምምነት መኖር አለበት የሚል አቋም ስታንጸባርቅ ቆይታለች፡፡
ግብጽ በአንጻሩ በ1950ዎቹ በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈረሙ ስምምነቶችን ጭምር በመጥቀስ ታሪካዊ የውሃ ድርሻየ ይቀንሳል የሚል አቤታቱ እያሰማች ነው፤የግድቡን መገንባትም ትቃወም ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ግን ይህ ስምምንት እንደማይመለከታት ገልጻለች፡፡
በየካቲት ወር በዋሸንግተን ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር በኢትዮጵያ ተቃውሞ ከተቋረጠ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት እንዲመራ ስምምነት ላይ ደርሰው፤ ድርድሩም በህብረቱ መሪነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡