ዋና ጸሃፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ “ለሰላም ወዳድ ሶማሊያውያን መጽናናትን እምኛለሁ” ብለዋል
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በሞቃዲሾ የተፈጸመውንና ለበርካታ ንጹሃን ሞት፣ ለትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች ውድመት ምክንያት አሰቃቂ የሽብር ጥቃት አወገዙ።
ዋና ጸሃፊው የተሰማቸውን ሀዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹ ሲሆን፤ ለሁሉም ሰላም ወዳድ ሶማሊውያን መጽናናትን እንዲሁም ለተጎዱት ቶሎ እንዲያገግሙ ተመኝቷል።
ኢጋድ ለሶማሊያ መንግስትም ሆነ ለሶሚያ ህዝብ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነውም ብለዋል ዋና ጸሃፊው ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ።
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሌሊት ላይ በደረሰው ፍንዳታ ከፍተኛ የፍንዳታ አደጋ ቢያንስ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ 17 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተነግሯል።
ሮይተርስ እማኙን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ፍንዳታው ከደረሰበት ቦታ ላይ የጭስ ይታይ ነበር እንደሁም የጥይት ድምጽ ሲሰማ ነበር ብሏል።
ለጥቃቱ እስካሁን ኃለፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም፤ አልሻባባ በተለያዩ ጊዜያት ከመፈጽማቸው ጥቃቶች ጋር በተያያዘ አልሻባብ ሊሆን እንደሚችል ይገማታል።
ሰኞ እለት የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል የታችኛው ሸበሌ ጠቅላይ ግዛት አፍጎዬ አከባቢ በአሸባሪው የአልሸባብ እንቅስቃሴ ላይ ልዩ ዘመቻ መፈጸሙ የሚታወስ ነው።
በዘመቻው የኦፊሴላዊው የሰራዊት ድምጽ ራዲዮ የስለላ አገልግሎቱ፤ ሶስት የአልሸባብ ንቅናቄ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማስታወቁም ጭምር ይታወቃል።
በቅርቡ የሶማሊያ መረጃና ደህንነት ክፍል፤ የአልሸባብን ጥቃት ቀድሞ ለመከላከል የሚያችሉ እንደ ፈንጂዎችን መያዝ፣ ጥቃትን ማክሸፍ እና ከመሪዎች እና የተለያዩ አካላት መካከል የአሸባሪ ድርጅት አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋልን የመሳሰሉ ዘመቻወችን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።