የፈረንጆቹ 2021 “በከፍተኛ ፈተናዎች የታጀበ ዓመት” እንደነበረ ኢጋድ ገለፀ
የኮሮና ወረርሽኝ፣ የአምበጣ ወረርሽኝ፣ ጎርፍና ሽብርተኝነት ቀጠናው ባለፈው ዓመት የገጠሙት ዋና ዋና ፈተናዎች ናቸው
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት፣ የሱዳን የሽግግር ሂደትና የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ጉዳይም የኢጋድ የዓመቱ አበይት አጀንዳዎች ነበሩ
የምሰራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን/ኢጋድ/ በመገባደድ ላይ ያለው የፈረንጆቹ 2021 በከፍተኛ ፈተና የታጀበ ዓመት እንደነበር ገለፀ
ኢጋድ ይህንን ያለው በኬንያ ሞምባሳ እያካሄደ ባለው ሁለተኛው ዓመታዊ ስብሰባው ላይ ነው።
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በመገባደድ ላይ ያለው የፈረንጆቹ 2021 ዓመት የአፍሪካ ቀንድ በርካታ ፈታናዎች ያስተናገደበት ዓመት ሆኖ ማለፉን በስብሰባው ተናግለዋል።
“የኮሮና ወረርሽኝ፣ የአምበጣ ወረርሽኝ፣ ጎርፍ እና ሽብርተኝነት” 250 ሚልን ህዝቦች የሚገኙበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ባለፈው ዓመት የገጠሙት ዋና ዋና ፈተናዎች መሆናቸውንም ዋና ጸሃፊው ገልጸዋል
እንደፈረንጆቹ 1996 የኢጋድ መስራቾች ባስቀመጡት ራዕይ መሰረት የቀጠናውን ሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማረጋጋጥ ኢጋድ የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን ያነሱት ዶ/ር ወርቅነህ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት፣ የሱዳን የሽግግር ሂደት እንዲሁም የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ጉዳይ የዓመቱ የኢጋድ አበይት አጀንዳዎች እንደነበሩም ገልጸዋል።
የምሰራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን/ኢጋድ/ የበሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነትን በዓመቱ እጅጉን ካሳሰቡት ጉዳዮች ውስጥ አነድ መሆኑን አስታውቋል።
የኢጋድ ዋና ጸኃፊ ዶ/ር ወርቅነህ፤ ኢጋድ እንደ ተቋም በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለመፍታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
የቀጠናው መሪዎች በኢትዮጵያ ያለው ችግር እንዲያበቃ ሲያደርጉት የቆየውንአስተዋጽኦም ዋና ጸኃፊ ዶ/ር ወርቅነህ አድንቀዋል።
“የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ፣የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ፎርማጆ እንዲሁም አፍሪካ ህብረትና የተለያዩ አምባሳደሮች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ ያደረጉትን ጥረት አደንቃለሁ” ብለዋል።
ለዘመናት የአፍሪካ የነጻነት ቀንዲል እና የሰላም ተምሳሌት፣ እንዲሁም የአፍሪካውያን መቀመጫ የሆነች ኢትዮጵያ ያጋጠማት የውስጥ ችግር የመፍታታ አቅም እንዳላት ኢጋድ በመሪዎቿና በህዝቦቿ ይተማመናልም ነው ያሉት ዋና ጸሃፊው።
የሱዳን ጉዳይ የኢጋድ የዓመቱ አብይ አጀንዳ ነበር ያሉት ዶ/ር ወርቅነህ፤ በተደረሰው የፖለቲካ ስምምነት መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ ስልጣናቸው መመለሰቻው የሚበረታታ ጅምር ነው ብለዋል።
የሱዳን የፖለቲካ መሪዎች ለህዝባቸው ፍላጎት ቅድሚያ እንደሚሰጡና በስምምነቱ መሰረት ስልጣን ወደ ሲቪል አገዛዝ የማስተላለፉ ሂደት እውን እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ኢጋድ የሱዳን የሽግግር ሂደት እንዲሳለጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ዋና ጸሃፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አረጋግጠዋል።
ኢጋድ በደቡብ ሱዳን የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ከሀገሪቱ መንግስት ጋር እየሰራ መሆኑንም ዶ/ር ወርቅነህ በንግግራቸው አንስተዋል።
የደቡብ ሱዳን አመራሮች ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት ዋና ጸሃፊው፤ የስምምነቱ ተግባራዊነት የተሟላ የሚሆነው በሽግግር የደህንነት መዋቅሩ የሚደረገውን ስብጥር እውን ማድረግ ሲቻል መሆኑን ተናግረዋል።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትን በተሟላ መልኩ ለመተግበር የሚያደናቅፉ “በሀገሪቱ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦችን” እንዲያነሳም ዋና ጸሃፊው ጠይቀዋል።
የምሰራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን/ኢጋድ/ ዋና ጸሃፊው ዶ/ር ወርቅነህ፤ “ሶማሊያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ያለች ሀገር ናት” ሲሉ በንግግራቸው አስታውቀዋል።
ሶማሊያ በቀጣይ የምታደርገው ምርጫ የሶማሊውያን እጣ-ፈንታ የሚወሰንበት ቁልፍ መድረክ በመሆኑ፤ ኢጋድም ሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሶማሊያን “ዴሞክራሲያዊ ምርጫ” ይጠብቃል ብሏል።
ሶማሊያውያን እንደ ኡጋንዳ፣ጁቡቲ እና ኢትዮጵያ የተሳካ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እና ተዓማኒ ምርጫ ማድረግ ይጠበቅባቿልም ነው ያሉት ዶ/ር ወርቅነህ።
እንደ ሶማሊያ ሁሉ ኬንያ ለምታካሂደው ምርጫ ኢጋድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጧል።
የቀጠናው ሰላምና ጸጥታ
ዋና ጸሃፊው ዶ/ር ወርቅነህ አፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ ኢጋድ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ መሆኑን መንግራቸው አክለው ገልጸዋል።
አልሸባብን ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ኃይሎች በቀጠናው ላይ የሚሰነዝሩት ጥቃት ባለፈው ዓመት እየከፋ መምጣቱን ያነሱት ዶ/ር ወርቅነህ፤ በዓመቱ በሶማሊያ፣ኬንያ እና ኡጋንዳ የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችም አውግዟል።
በሽብር ጥቃቶቹ ምክንያት ህይወታቸው ባለፈ ዜጎች ኢጋድ ጥልቅ ሀዘን እንደተሳማውና ለቤተሰቦቻቸው መጥናናትን እንደሚመኝም ዋና ጸሃፊው ገልጸዋል።
ሽብረተኝነት ዓለም አቀፍ ስጋት እንደሞሁኑ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።