ሰላት እየመሩ ድመት የወጣችባቸው ኢማም ስለ ሁኔታው ምን አሉ?
በአልጀሪያ የተራዊህ ሰላት ስነ ስርዓት በመምራት ላይ በነበሩ ሼክ ትከሻ ላይ የወጣችው ድመት መነጋገሪያ ሆናለች
ሼክ ዋሊድ ሜህሳስ “ፈጣሪ ይመስገን ሃይማኖታች ለእንስሳት የዋህ እንድንሆን የሚያዘን ነው” ብለዋል
ከሰሞኑ በአልጀሪያ የተራዊህ ሰላት ስነ ስርዓት ላይ አንዲት ድምት መታየቷ እና በሰላቱ ላይ የተከሰተው ነገር የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
ይህም የተራዊህ ሰላት ስነ ስርዓት በመምራት ላይ በነበሩ ሼክ ዋሊድ ሜህሳስ ትከሻ ላይ ድመት መውጣቷን የሚያሳይ ቪዲዮ መለቀቁን ተከትሎ ነው።
ድመቷ ከመሬት ላይ ዘላ የሼክ ዋሊድ ሜህሳስ ትክሻ ላይ የወጣች ሲሆን፤ ሰላቱን ሲመሩ የነበሩት ኢማምም ሰላታቸውን ሳያቋርጡ ድመቷ እንዳትወድቅ ስደግፉ የሚያሳይ ነበር።
ይህንን ተከትሎም መነጋገሪያ የሆኑትን ሼክ ዋሊድ ሜህሳስን የአልጄሪያ የኃይማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ተቀብለእንዳነጋገሯቸውም ተነግሯል
ሼክ ዋሊድ ሜህሳስ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩም፤ “በፌስቡክ ቪዲዮዋቸው ላይ የተለቀቀው ቪዲዮ ያልታሰበ እና አስገራሚ ነገር ነበር” ብለዋል።
“ክስተቱ ያልተጠበቀ ነበር፤ ፈጣ ይመስገን ኃይማኖታችን ለእንስሳት የዋህ እንድንሆን የሚያዘን ነው” ሲሉም ነው ሼክ ዋሊድ ሜህሳስ የተናገሩት።
ሼክ ዋሊድ ሜህሳስ አክለውም በስማቸው ሀሰተኛ ፌስቡክ ገጽ የተከፈቱ ሰዎች በአፋጣን እንዲያጠፉት አለበለዚያ ግን ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስዱትም ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት አስተላልፈዋል።