አይኤምኤፍ 11 የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ገለጸ
አይኤምኤፍ ከአለም ባንክ፣ከኢንተር አሜሪካን ዴቨሎፕመንት ባንክ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር እንደሚሰራ ዳሬክተሯ ተናግረዋል
አይኤምኤፍ በሚያደርጋቸው የፋይናንስ ስራዎቹ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ከግምት እንደሚያስገባ ክሪስታሊና ጆርጂቫ ተናግረዋል
አይኤምኤፍ 11 የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ገለጸ።
የአለምአቀፉ የገንዝብ ፈንድ(አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጅቫ በአንድ አመት ውስጥ 11 የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሯ የአየር ንብረት ለውጥን መዋጋት የኢኮኖሚ መረጋጋትን እና አረንጓዴ ልማት ለማምጣት ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዳሬክተሯ ይህን ያሉት በአረብ ኢምሬትስ ዱባይ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ስብሰባ(ኮፕ28) ስብሰባ ላይ ነው።
በስብሰባው ላይ አይኤምኤፍ በሚያደርጋቸው የፋይናንስ ስራዎቹ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ከግምት እንደሚያስገባ ክሪስታሊና ጆርጂቫ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሯ "ዘላቂነትን በማምጣት ረገድ ግባችንን አሳክተናል። ከአረብ ኢምሬትስ የተዋጣውን ጨምሮ 41ቢሊዮን አለን። በአንድ አመት ውስጥ ከተሳኩት 11 ፕሮጀክቶች ውስጥ 6 በአፍሪካ የሚገኙ እና ለመጠናቀቅ ከሶስት እስከ አራት ወራች የሚፈጅባቸው ናቸው" ብለዋል።
አይኤምኤፍ ከአለም ባንክ፣ከኢንተር አሜሪካን ዴቨሎፕመንት ባንክ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር እንደሚሰራ ዳሬክተሯ ተናግረዋል።
ከ198 ሀገራት በላይ የተወከሉበት የኮፕ28 ስብሰባ ዛሬ አምስኛ ቀኑን ይዟል።