አይ.ኤም.ኤፍ የትግራይን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተለው ነው-ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ
የተከሰተው ቀውስ ከሰብኣዊ እርዳታ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው
ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጫናውን ተቋቁማ መቀጠል እንድትችል አይ.ኤም.ኤፍ አስፈላጊውን ምክረ ሀሳብ ይሰጣል
በትግራይ ክልል ያጋጠመውን ሰብአዊ ቀውስ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ.ኤም.ኤፍ) በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ ተናገሩ፡፡
ዳይሬክተርዋ ከToday News Africa’s የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዘጋቢ ሳይሞን አቴባ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ እንዳሉት ከሆነ፤ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ቀውስ ከሰብኣዊ እርዳታ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል፡፡
“የትግራይ ጉዳይ ያሳስበናል” እናም ያለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልነው ነው፤ በእንደዚህ አይነት ሰብአዊ ቀውስ ዜጎች ያልተገባ ዋጋ ሊከፍሉ አይገባም’ም ሲሉም ተናገረዋል የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ.ኤም.ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ፡፡
ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ አሁን በሀገሪቱ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሁኔታና የሚፈጥረው ተፅእኖ ድርጅታቸው አይ.ኤም.ኤፍ በትኩረት እየተከታተለው መሆኑ በመናገር፤ ሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጫናውን ተቋቁማ መቀጠል እንድትችል አስፈላጊውን ምክረ ሀሳብ ለመስጠት ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ማኔጂንግ ዳይሬክተርዋ የኢትዮጵያ ጥሩ መሆን ለተቀረው አህጉረ አፍሪካ ወሳኝ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡