አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ሲያደርገው የነበረው ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ገለጸ
የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ሲወያዩ መክረዋል
ተቋሙ የመጨረሻ ውሳኔውን በዋሸንግተን ተጨማሪ ውይይት ካደረገ በኋላ ገንዘቡን ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል
አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ሲያደርገው የነበው ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ገለጸ፡፡
ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ደጋፍ ከሚያደርጉ የገንዘብ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ውይይት በመደረግ ላይ ነው፡፡
የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ሲመክር መቆየቱን ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በመግለጫው እንዳለው በአልቫሮ ፒሪስ የተመራው ቡድን በአዲስ አበባ ስለነበረው ጉብኝት እና ውይይት ዙሪያ እንዳሉት ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ባንኩ በአዲስ አበባ ቆይታው ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ያደረገው ውይይት ለውጥ የታየበት ነበር ያለው ድርጅቱ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል ኢኮኖሚ እቅድ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል፡፡
ለረጅም ቀናት በቆየው የአይኤምኤፍ እና ኢትዮጵያ ውይይት ገና ፍጻሜ ያላገኘ ሲሆን ቀጣይ ውይይቶች በዋሸንግተን እንደሚደረጉ ድርጅቱ ገልጿል፡፡
አይኤምኤፍ እና አለም ባንክ በዋሸንግተን በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝተው እንደሚወያዩ የተገለጸ ሲሆን ከውይይቶች በኋላ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ስለሚሰጠው ብድር መጠን ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በፈረንጆቹ 2018 ላይ አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ አንደሚደግፍ የገለጸ ቢሆንም በሰሜን ኢትዮያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ድጋፉ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
የፌደራል መንግስት እና ህወሃት ጦርነቱን ለማቆም በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ በርካታ ሀገራት እና የገንዘብ አበዳሪ ተቋማት ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ በጦርነቱ እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መጎዳቱን ተከትሎ አበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት የብድር መክፈያ ጊዜን እንዲያራዝሙ በይፋ የጠየቀች ሲሆን ውይይቶችም እንደቀጠሉ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡