ሞሮኮ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ሩብ ፍፃሜን ተቀላቀለች 4ኛ አፍሪካዊት ሀገር ነች
የአትላስ አንበሶቹ ሞሮኮዎች በትናንትናው እለት ስፔንን በመርታት በታካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን ተቀላቅላለች።
ሁለቱም የጨዋታ አጋማሾችና ተጨማሪው 30 ደቂቃ ያለግብ በመጠናቀቁ በተሰጠ የመለያ ምት ነው ሞሮኮ አሸንፋ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለችው።
የአትላስ አንበሶቹ የ2010 የአለም ዋንጫ ሻምፒዮኗን ሰፔን ፈትነዋት አምሽተዋል። ከአራት አመት በፊት በአለም ዋንጫው የተገናኙት ሁለቱ ሀገራት 2 ለ 2 ተለያይተው እንደነበር ይታወሳል።
በሚያስቆጩ የጎል ሙከራዎች የታጀበው የዛሬው ፍልሚያም በአቻ ውጤት ተጠናቆ በመለያ ምት ጥሎ ማለፉን የሚቀላቀለው ተለይቷል።
ቤልጂየምን 2 ለ 0 በመርታት ከምድብ ያሰናበተቻት ሞሮኮ በአስደናቂ ደጋፊዎቿ ደምቃ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።
በ92 አመት የአለም ዋንጫው ጉዞ ግማሽ ፍፃሜ የደረሰ አንድም የአፍሪካ ቡድን ግን የለም፤ ሩብ ፍፃሜ የደረሱም ሞሮኮን ጨምሮ ሀገራት ናቸው።