ሚሳዔሉ በጥገና ላይ ሳለ ባጋጠመ የቴክኒክ ስህተት በድንገት መወንጨፉን ህንድ አስታውቃለች
ህንድ በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳኤል አስወነጨፈች፡፡
የሩቅ ምስራቋ ህንድ በስህተት ወደ ጎረቤቷ ፓኪስታን ሚሳኤል ማስወንጨፏን አስታውቃለች፡፡
ህንድ ሚሳኤሉን ያስወነጨፈችው የቴክኒክ ባለሙያዎች የጥገና ስራ ለመስራት በተንቀሳቀሱበት ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ህንድ በስህተት ባስወነጨፈችው ሚሳኤል መጸጸቷን የገለጸች ሲሆን ለተፈጠረው ስህተት የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር በኩል ይቅርታም ጠይቃለች፡፡
ሚሳዔሉ ለጊዜው ስሙ ባልተጠቀሰ የፓኪስታን ግዛት ማረፉን የሃገሪቱ መከላከያ አስታውቋል፡፡ ያጋጠመው ነገር እጅግ የሚያጸጽት ቢሆንም ሰብዓዊም ሆነ ቁሳዊ ጉዳት አለማድረሱ ደግሞ ትልቅ ነገር እንደሆነም ነው መከላከያው የገለጸው፡፡
ጉዳዩን በህግ መያዙንም የሃገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡
የፓኪስታን መከላከያ ሃይል ከህንድ የተተኮሰበትን ሚሳኤል አቅጣጫ በማስቀየር አደጋ እንዳያደርስ ማድረጉን ገልጿል፡፡
የኑክሌር አረር ባለቤት የሆኑት ህንድ እና ፓኪስታን በካሽሚር ግዛት ይገባኛል በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ በተደጋጋሚ ወደ ለየለት ጦርነት ይገባሉ የሚሉ ስጋቶች እንዳለ ነው፡፡