ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ያሉት ሩሲያ እና ቻይና ድንበር ተሻጋሪ ድልድይ ከፈቱ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት መክፈቷን ተከትሎ ምእራባውያን በሩሲያ ላይ ማእቀብ ጥለዋል
ሩሲያ የዶማባስ ግዛትን ነጻ እስከምታወጣ ድረስ ጦርነት እንደሚቀጥል ገልጻለች
ሩሲያ እና ቻይና በሩቅ ምስራቅ አዲስ ድንበር አቋራጭ ድልድይ ከፍተዋል፡፡
የድልድዩ መከፈት ሩሲ በዩክሬን ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት በምእራባውያን የተጣለባን ማእቀብ እንድትቋቋም እና የንግድ እንቅስቃሴዋ እንዲያድግ ይረዳታል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በአሙር ወንዝ ላይ የተገነባው እና አንድ ኪሎሜትር የሚደርሰው ድልድይ የሩሲያዋን ቫላጎቨሸንሽኪን እና የቻይናዋን ሐይ ከተማ ያገናኛል፡፡ ድልድዩን ለመገንት 342 ሚሊዮን ዶለር መፍሰሱን ሮይተርስ ሪያ ዜናገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በድልድዩ መርቃት ወቅት ከሁለቱም ጫፍ የተነሱ የጭነት መኪናዎች የሁለቱም ሀገራት ባንዲራ ያጌጠ ድልድይ ባለ ሁለት መስመር ድልድይ ሲያቋርጡ ተስተውለዋል ብሏል ዘገባው፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ከመላካቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በየካቲት ወር ላይ ከቻይና"ምንም ገደብ" የለም የሚል አጋርነት ካወጁ በኋላ ድልድዩ ሞስኮ እና ቤጂንግ የንግድ ልውውጥን በማሳደግ ያቀራርባል ብለዋል የሩሲያ ባለስልጣናት።
በሩሲያ የሩቅ ምስራቅ የክሬምሊን ተወካይ ዩሪ ትሩትኔቭ "በአሁኑ በተከፋፈለው ዓለም በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው የብላጎቬሽቼንስክ-ሄሄ ድልድይ ልዩ ምሳሌያዊ ትርጉም አለው" ብለዋል ።
ሩሲያ በላፈው የካቲት ወር በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ጥቃት የከፈተችው ምእራባውያን ዩክሬንን የኔቶ አባል ለማድግ እየተንቀሳቀሱ ነው፤ይህም ለደህንነቴ ያሰጋኛል በሚል ነበር፡፡
ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ሩሲያ ዩክሬን ወደ ሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) እንዳትቀላቀል ማስጠንቀቂያ ስትሰጥ መቆየቷ ይታወሳል፡፡ በምእራባውያን የምትደገፈው ዩክሬን ግን ይህን ማስጠንቀቂያ አልተቀበለችውም ነበር፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ሩሲያ ያዳክማል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ማእቀብ ጥለዋል፤እየጣሉም ይገኛሉ፡፡
ሩሲያ ወዳጅ አይደሉም ያለቻቸው ምእራባውያን ሀገራት ነዳጇን በሩብል እንዲገዙ በማድረግ የተጣለባትን ማእቀብ ለመበቀል ሞክራለች፤ በዚህም የተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያ ፍላጎት ነጃጅ እየገዙ ነው፡፡
የአውሮፓ ህብረትም የነዳጅ ገዥ ኩባንያዎች በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማእቀብ በማይጻረር ምልኩ ነዳጅ በሩብል ምዛት ይችላሉ ማለቱም ይታወሳል፡፡
ጦርነቱ አሁንም በመካሄድ ላይ ሲሆን ሩሲያ የዶምባስ ግዛት ነጻ እስከሚወጣ ድረስ ይቀጥላል ብላለች፡፡