የህንድ ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሟል የተባለ ግለሰብን ቤት አቃጠሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ እርምጃ እንደሚወስዱ ከተናገሩ ከሰአታት በኋላ ዋና ተጠርጣሪ የሆነው የማኒፑር ነዋሪ በቁጥጥር ስር ውሏል
ወሲባዊ ጥቃቱ የተፈጸመው ከሁለት ወራት በፊት ቢሆንም ክስተቱን የሚያሳይ ቪዲዮ ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ መለቀቁን ተከትሎ ነው ትኩረት ያገኘው
በሰሜን ምስራቅ ህንድ በምትገኘው ማኒፑር ግዛት ሴቶች ሀገሪቱን ባስቆጣው ወሲባዊ ጥቃት ተሳትፏል የተባለውን የዋና ተጠርጣሪውን ግለሰብ ቤት አቃጥለዋል።
ግለሰቡ ባለፈው ግንቦት ወር ሁለት ሴቶችን ጎትቶ ወደ አደባባይ በማውጣት ሌሎች ሰዎች በቡድን እንዲደፍሯቸው እና እርቃናቸውን እንዲታዩ ማድረጉን ፖሊስ ገልጿል።
ወሲባዊ ጥቃቱ የተፈጸመው ከሁለት ወራት በፊት ቢሆንም ክስተቱን የሚያሳይ ቪዲዮ ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ መለቀቁን ተከትሎ ነው ትኩረት ያገኘው።
ክስተቱ በማኒፑር ግዛት አለመረጋጋትም አስከትሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጥቃቱን "አስነዋሪ" ብለው ካወገዙ እና እርምጃ እንደሚወስዱ ከተናገሩ ከሰአታት በኋላ ዋና ተጠርጣሪ የሆነው የማኒፑር ነዋሪ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ተጨማሪ ሶስት ተጠርጣሪዎች የተያዙ ሲሆን በጥቃቱ ተሳትፈዋል የተባሉ 30 ሰዎችን በመከታተል ላይ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
"የአካባቢው ሴቶች የዋና ተጠርጣሪውን ቤት በድንጋይ መትተዋል። የተወሰነውን የቤቱን ክፍልም አቃጥለዋል" ሲሉ የግዛቷ ዋና ከተማ ኢምፖላ ከፍተኛ የፖሊስ ኃላፊ ሄማንት ፖንዲ ተናግረዋል።
ኋላፊው "ድርጊቱ የሚያበሳጭ በመሆኑ ሴቶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን እንዲገልጹ ጠይቀናል። ብስጭታቸውን እንረዳለን ብለዋል።" ሲሉ ተናግረዋል።
ባለፈው ግንቦት ወር ለፖሊስ የቀረበ ቅሬታ እንደሚያመለክተው የታጠቁ ሰዎች የኩኪ ጎሳ አባላትን ከማጥቃታቸው በፊት የተወሰኑ ቤቶችን መዝረፋቸውን እና ማቃጠላቸውን ይጠቅሳል።
በወቅቱ የቀረበው ቅሬታ የ21 እና 19 አመት እድሜ ያላቸው ሴቶች በቡድን መደፈራቸውን ይገልጿል።
ማኒፑሮ ግዛት ለ125 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የጎሳ ግጭት በተከሰተበት ግንቦት ወር የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ሴቶች ቅሬታ አሰምተው ነበር።