ህንድ በቻይናና በፓኪስታን አቅራቢያ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ልታሰማራ ነው
የህንድና ቻይና ወታደሮች በአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ በተደጋጋሚ መጋጨታቸው ይታወቃል
ህንድ ከዚህ ቀደም በስህተት ወደ ጎረቤቷ ፓኪስታን ሚሳኤል አስወንጭፋ ነበር
ህንድ ከቻይና እና በፓኪስታን ጋር በሚያዋስኗት ድንበሮች አቅራቢያ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ልታሰማራ መሆኑ ከሰሞኑ ተሰምቷል።
የኑክሌር አረር ባለቤት የሆኑት ህንድ እና ፓኪስታን በካሽሚር ግዛት ይገባኛል በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ በተደጋጋሚ ወደ ለየለት ጦርነት ይገባሉ የሚሉ ስጋቶች እንዳለ ነው።
በተጨማሪም ህንድ ህንድ ከቻይና ጋር በድንበር ይገባኛል ውዝግብ ውስጥ ያለች ሲሆን፤ የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ወታደሮች በአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ በተደጋጋሚ መጋጨታቸው ይታወቃል።
ህንድ ከቻይና እና ከፓኪስታን ጋር በሚያዋስናት ድንበር እቅራቢያ ከሰሞኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን ለማሰማራት ማቀዷን ኤ.ኤን.አይ የተባለ የሀገሪቱ የዜና ተቋም ዘግቧል።
ህንድ ሚሳዔሎችን ድንብር አካባቢ ልታሰማራ ነው የሚለው ሪፖርት የወጣው በያዝነው ወር በሂማሊያ አካባቢ በህንድ እና በቻይና ወታደሮች መካከል ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ እንደሆነም ተዘግቧል።
የህንድ የመከላከያ ምንጮች ለኤ.ኤን.አይ የዜና ተቋም በሰጡት መረጃም” የህንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ከሰሞኑ ባደረጉት ስብሰባ 120የባላስቲክ ሚሳዔሎች ለህንድ ወታደሮች አንዲሰጡ እና ድብር አካባቢ እንዲሰማሩ ወስነዋል” ብለዋል።
የሕንድና ቻይና ወታደሮች በአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ ከሰሞኑ ተጋጭተው በወታደሮች ላይ ጉዳጥ መድረሱ ይታወሳል።
በተያያዘ ህንድ በካሽሚር ግዛት ይገባኛል ጋር በተያያዘ ወደምትወዛገባት ፓኪስታን በስህተት ወደ ጎረቤቷ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ይታወሳል።
የኑክሌር አረር ባለቤት የሆኑት ህንድ እና ፓኪስታን በካሽሚር ግዛት ይገባኛል በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ በተደጋጋሚ ወደ ለየለት ጦርነት ይገባሉ የሚሉ ስጋቶች እንዳለ ነው።