ባለጸጋው፥ ጥቃቱ በእሳቸው እና በሕንድ ላይ የተፈጸመ "የቅኝ ገዢዎች ተንኮል" መሆኑን ተናግረዋል
ህንዳዊው ቢሊዬነር በአንድ ሳምንት ውስጥ 100 ቢሊዮን ዶላር ከሰሩ፡፡
ጓታም አዳኒ ከአንድ ሳምንት በፊት በፈረንሳዊው የፋሺን ሰው በርናርድ አርናልት እና በአሜሪካዊው ኢለን መስክ ተበልጠው ሶስተኛው የዓለማችን ቢሊዬነር ነበሩ፡፡
የ200 ቢሊዮን ካፒታል የሚያንቀሳቅሱት እኝህ ህንዳዊ በወደብ አገልግሎት፣ በድንጋይ ከሰል፣ በሚዲያ ቴክኖሎጂ፣ በኬሚካል እና ኤርፖርቶች አስተዳድር የተሰማሩ ዓለም አቀፉ ኩባንያዎችም አሏቸው፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ንግድ የገቡት እና ከሕንዷ ጉጃራት ግዛት የተገኙት ጓታም አዳኒ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኢንቨስትመንት ሰው ናቸው፡፡
ይሁንና ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ ሂልበርግ የተሰኘ የጥናት ተቋም በአዳኒ ኩባንያ ላያ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ ነበር ችግር መፈጠር የጀመረው፡፡
ይህ የአሜሪካ ተቋም በሪፖርቱ አዳኒ ኢንተርፕራይዝ ግብር እንደማይከፍል፣ ገንዘብ እንደሚደብቅ እና ሌሎች ህገወጥ ስራዎችን እንደሚያከናውን ይፋ አድርጓል፡፡
ይሄንን ሪፖርት ተከትሎም በአዳኒ ኢንተርፕራይዝ ስር ባሉ ኩባንያዎች ውስጥ ያለው የአክስዮን ዋጋ በፍጥነት መቀነስ ይጀምራል፡፡
በጥቂት ቀናት ውስጥም አዳኒ ኢንተርፕራይዝ 100 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስመዝገቡን ነው ሬውተርስ የዘገበው።
ኪሳራውን ተከትሎም ጓታም አዳኒ በሶስተኛ ከተቀመጡበት የዓለማችን ቢሊየነርነት ደረጃ ማሽቆልቆላቸው ሲገለጽ የሀብት መጠናቸውም ከ127 ቢሊዮን ዶላር ወደ 27 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱ ተገልጿል፡፡
ጓታም አዳኒ በበኩላቸው የአሜሪካው ኩባንያ ያወጣውን ሪፖርት በእሳቸው እና በሕንድ ላይ ቅኝ ገዢዎች የፈጸሙት ጥቃት አድርገው ወስደውታል፡፡
ባለጸጋው ጓታም አዳኒ ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ስላላቸው ግዙፍ ጨረታዎችን በቀላሉ ያገኛሉ፤ ሌሎች ድጋፎችም ይደረግላቸዋል የሚል ወቀሳ እንደሚቀርብባቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡