የህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ ጥቅጥቅ ባለ ጭጋግ ስትሸፈን፣ በረራ ሊስተጓጎል ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል
የአቪየሺን ራዳር 24 መረጃ እንደሚያሳየው በ 20 በረራዎች ውስጥ በአማካኝ የስምንት ደቂቃ መዝግየት ተመዝግቧል።
የሀገሪቱ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ተቋም እንደገለጸው በዛሬው እለት ያለው የኒው ዴልሂ የአየር ሁኔታ "በጣም ዝቅተኛ" የሚባል ነው ብሏል
የህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ በወፍራሙ ጭጋጋ በመሸፈኗ ምክንያት የአውሮፕላን በረራን ሊያስተጓጉል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
በዋና ከተማዋ ላይ የተከሰተው ጭጋግ በአንዳንድ ቦታዎች ያለውን እይታ ወደ ዜሮ በማውረዱ ምክንያት ኤየርፖርቶች እና አየርመንገዶች የበረራ መስተጓጎል ሊኖር ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ ማሰማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ክረምት ከገባ ጀምሮ ጭጋግን እና ዝቅተኛ የአየር ጥራት ሁኔታን እየተዋጋች ያለችው ዴልሂ ስዊስ ግሩፕ አይኪውኤየር በዛሬው እለት ባወጣው ደረጃ መሰረት ዴልሂ በአለም በከፍተኛ መጠን ከተበከሉ ዋና ከተሞች ውስጥ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የህንዱ ግዙፍ አየርመንገድ ኢንዲጎ እና በአነስተኛ ዋጋ አገልግሎት የሚሰጠው ስፓይስ ጄት በአየር ሁኔታው ምክንያት የበረራ መዘግየት ሊኖር እንደሚችል ገልጿል።
የአቪየሺን ራዳር 24 መረጃ እንደሚያሳየው በ 20 በረራዎች ውስጥ በአማካኝ የስምንት ደቂቃ መዝግየት ተመዝግቧል።
የሀገሪቱ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ተቋም እንደገለጸው በዛሬው እለት ያለው የኒው ዴልሂ የአየር ሁኔታ "በጣም ዝቅተኛ" የሚባል ነው ብሏል።
ህንድ እና ፖኪስታን በከፍተኛ መጠን የተበከሉ ከተሞች ካሏቸው የአለም ሀገራት መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው።