እርጅናን እናስቀራለን በሚል ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ያጭበረበሩት ባልና ሚስቶች
ግለሰቦቹ ከሀገር እንዳይወጡ ክልከላ ቢጣልባቸውም አስቀድመው ወደ ሌሎች ሀገራት እንደሸሹ ተገልጿል
ባልና ሚስቶቹ ከ24 በላይ ሰዎችን አሁን ካሉበት የእርጅና እድሜ ወደ ወጣትነት እንመልሳለን በሚል አጭበርብረዋል ተብሏል
እርጅናን እናስቀራለን በሚል ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ያጭበረበሩት ባልና ሚስቶች
ራጂቭ ኩማር እና ራሽሚ ዱቤይ የተባሉት ህንዳዊያን ባልና ሚስቶች ሲሆኑ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እርጅናቸው የተፋጠነባቸውን ሰዎች ወደ ወጣትነት እድሜ መመለስ የሚያስችል ህክምና እንደጀመሩ ይናገራሉ፡፡
እነዚህ ባልና ሚስቶች በእስራኤል ሀገር በተማሩት ሙያ እና ባስመጡት የቴራፒ ህክምና አማካኝነት ብዙ ደንበኞችን ያተርፋሉ፡፡
ህክምናው በተለያዩ ዙሮች በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚሰጡ የሚናገሩት እነዚህ ጥንዶች ከ24 በላይ ሰዎችን እንዳጭበረበሩ ተገልጿል፡፡
21 ሺህ ዶላር የተጭበረበረ አንድ አመልካች ለፖሊስ እንዳለው ከሆነ ህክምናው ለዓመታት እንደሚሰጥ እና ለውጡን ለማየት ዓመታት እንደሚፈጅ ከነገሩት በኋላ በተለያዩ ዙሮች ክፍያዎችን ሲከፍል እንደቆየ ተናግሯል፡፡
አዲስ ደንበኛ ካመጣህ ክፍያ ይቀንስልሃል እንደሚባል የጠናገረው ይህ ተጎጂ እሱ አሳምኗቸው ህክምናውን የጀመሩ ሰዎች እያስፈራሩኝ ነውም ብሏል፡፡
የጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ የኢስዋትኒ ንጉስ 16ኛዋ ሚስት በመሆን ተሞሸረች
ባልና ሚስቶቹ በሚሰጡት ህክምና ከእርጅና ላይ 20 ዓመት እና ከዛ በላይ ወደ ወጣትነቱ እንደሚመለስ ተነግሮት ህክምናውን እንደጀመረ የተናገረ ሌላኛው ተጎጂ በበኩሉ በ10 ዙር 720 ዶላር እንደከፈለ ተናግሯል፡፡
ባልና ሚስቶቹ እርጅናን ከማስቀረት ባለፈ የተጎዱ የሰውነት ውስጣዊ አካላትን ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንደሚመልሱም ለደንበኞቻቸው ሲናገሩ ነበር ተብሏል፡፡
የህንድ ፖሊስ ተጭበረበርን ባሉ ዜጎች ዙሪያ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ክስ በቀረበባቸው ባልና ሚስቶች ላይ የጉዞ እገዳ ማውጣቱን አስታውቋል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ይሁንና ባልና ሚስቶቹ ከ24 በላይ ከሆኑ ሰዎች 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ካጭበረበሩ በኋላ እገዳው ከመውጣቱ በፊት ህንድን ለቀው ወጥተዋል ተብሏል፡፡