ሚስት ያገኘ መስሎት 85 ሺህ ፓውንድ የተታለለው እንግሊዛዊ
የቀድሞው የተመድ ሰራተኛ የሆነው ይህ እንግሊዛዊ ያለውን ገንዘብ ሁሉ ከላከ በኋላ እንደታለለ አውቋል
ከሚስቱ ጋር በኬንያ ሊኖር አስቦ የነበረው ሰው በመጨረሻም የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን ተገዷል
ሚስት ያገኘ መስሎት 85 ሺህ ፓውንድ የተታለለው እንግሊዛዊ
ሮድሪክ ሎጅ የተባለው እንግሊዛዊ የ69 ዓመት እድሜ ያለው ሲሆን የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛም ነበር፡፡
ይህ ሰው ከዚህ በፊት ባለ ትዳር የነበረ ሲሆን ባለቤቱ በፈረንጆቹ 2019 ላይ ነበር ህይወቷ ያለፈው፡፡
ሚስቱ ከሞተች በኋላ ብቻውን መኖር የከበደው ይህ ሰውም በአንድ ጓደኛው አማካኝነት አንድ ኬንያዊት ይተዋወቃል፡፡
አኒታ የሚል ስም እንዳላት የተገለጸችው ይቺ ኬንያዊት ጋርም ቀስ በቀስ እየተግባቡ ሄደው እና በመጨረሻም በፍቅር ይወድቃሉ፡፡
በሩጫ ፍቅር ምክንያት ትዳሩ የፈረሰበት አባወራ…
ኬንያዊቷ በናይሮቢ የውበት መጠበቂያ መደብር እንዳላት እና 30 ሰራተኞችን እንደምታስተዳድር እንደነገረችውም ይህ ሰው ተናግሯል፡፡
ፍቅራቸው ቀስ በቀስ የደራው እነዚህ ጥንዶች ለመጋባት መወሰናቸውን ተከትሎ መኖሪያ ቤታቸውን ለማዘመን ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት ትነግረዋለች፡፡
ለረጅም ዓመት በተመድ ተቀጥሮ ሲሰራ ያጠራቀመውን ገንዘብ ለወደፊት ሚስቱ የላከው ይህ ሰውም ለመጋባት የጉዞ ቲኬት ቆርጦ ጉዞውን ወደ ኬንያ ናይሮቢ ያደርጋል፡፡
በጀሞ ኬንያታ ኤርፖርት አበባ ይዛ እንደምትጠብቀው የሚያውቀው ሮድሪክ ሎጅ አኒታን ከአውሮፕላን እንደወረደ ቢፈልጋትም ያጣታል፡፡
ከዚያች ዕለት ጀምሮ ደብዛዋ የጠፋችው አኒታ በመጨረሻም ባደረገው ክትትል አኒታ የምትባል ሴት እንደሌለች ያን ሁሉ ገንዘቡን እና ጊዜውን ሲበዘበዝ የነበረው ጓደኛው መሆኑን ይደርስበታል፡፡
ፍቅርን ብሎ የመጣው ሮድሪክ ሎጅም ወደ ሀገሩ እንግሊዝ ተመልሶ ቤት አልባ ሆኖ እየኖረ ሲሆን አንድም ሰው የሚረዳው እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡
“አንተ ደደብ እያሉ የሚጠሩ ጓደኞች አሉኝ፣ ምንም አድርገውልኝ አያውቁም በዚች ምድር ብቻዬን ሆኜ የጎዳና ተዳዳሪ ሆኞ እየኖርኩ ነው” ብሏል፡፡