የህጻን ጾታ ለማወቅ የሚስቱን ሆድ የቀደደው ህንዳዊ በፖሊስ ተያዘ
የህጻን ጾታ ለማወቅ የሚስቱን ሆድ የቀደደው ህንዳዊ በፖሊስ ተያዘ
በሰሜናዊ ህንድ የሚገኝ አንድ ሰው የህጻን ጾታ ለማወቅ የሚስቱን ሆድ በማጭድ ቀዶ ህጻኑ እንዲሞትና ሚስቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንድትጎዳ ካደረገ በኋላ በፖሊስ መያዙን ፖሊስና ዘመዶቿ ተናግረዋል፡፡
ጉዳት የደረሰባት ሚስት በህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ በሚገኝ ሆስፒታል ከፍተኛ እንክብካቤ እየተደረገላት መሆኑን በሰሜናዊ ኡታራ ፕራደሽ ግዛት ውስጥ ያለ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የሚስትዮዋ ወንድም እንደተናገረው ጥቃቱ የተፈጸመው ባል የህጻን ጾታ ለማወቅ በመፈለጉ ነው ብሏል፡፡ ጥንዶቹ ከዚህ በፊት አምስት ልጆች ያፈሩ ናቸው፡፡
“በማጭድ በማጥቃት ሆዷን ቀዷል፤ ይህን ያደረገው ያልተወለደውን ህጻን ጾታ ለማወቅ መሆኑን እንደተናገረ“ የሚስት ወንድም የሆነው ጎሉ ሲንህ ለሮይተርስ ተናግሯል፡፡
ፖሊስ እንደገለጸው ህፃኑ ሞቶ የተወለደ ሲሆን ይህን የፈጸመው ባል በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ይገኛል፡፡
በህንድ ሴት ልጆች ብዙ ጊዜ እንደጫና የሚቆጠሩና በጋብቻ ጊዜ ቤተሰብ ለጥሎች የሚከፍል ሲሆን ወንዶች በአንጻሩ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንዲሁም የቤተሰብን መልካም ስም የሚያስጠሩና ሀብት የሚወርሱ ናቸው፡፡
በህንድ የጽንስ ማስወረድ በህግ የተከለከለ ሲሆን የወንድ ልጆች ምርጫ መኖሩ የሴቶች ቁጥር እንዲቀንስ አድጓል፡፡