የህንድ ፖሊስ ለተቃውሞ ወደ ዴልሂ እያቀኑ ያሉ አርሶ አደሮችን ለማስቆም አውራ ጎዳናዎችን ዘጋ
በሰሜናዊ ህንድ ከፍተኛ ምርት በማምረት የሚታወቁት የፑንጃብ እና ሀርያና ግዛት አርሶ አደሮች ትራክተር እየነዱ ወደ ዴልሂ ሲጓዙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ወጥተዋል
ፖሊስ በአጥር ሽቦ፣ በሲሚንቶ ኮንክሪት እና በሌሎች ቁሶች አርሶ አደሮቹ ዘልቀው እንዳይገቡ የዴልሂ ከተማ ዳርቻ እየዘጋ ነው ተብሏል
የህንድ ፖሊስ ለተቃውሞ ወደ ዴልሂ እያቀኑ ያሉ አርሶ አደሮችን ለማስቆም አውራ ጎዳናዎችን ዘግቷል።
የህንድ ፖሊስ በፈረንጆቹ 2021 ቃል የተገባላቸው የእህል ዋጋ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲደረግ ጫና ለማድረግ ወደ ዴልሂ እያቀኑ የነበሩ አርሶ አደሮችን ለማስቆም መንገድ ዘግቷል።
ለአንድ አመት የዘለቀው ተቃውሞ በድጋሚ እንዳይቀሰቀስ የተወሰኑ የመንግስት ባለስልጣናት የግብርና ማህበራት መሪዎችን ሊያናግሩ እንደሚችሉ ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ የአርሶ አደሮች ሰልፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሶስተኛ ዙር የስልጣን ዘመን የሚወዳደሩበት ምርጫ ሊካሄድ ወራት ሲቀሩት የተደረገ ነው።
በህንድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች አርሶ አደሮች ሲሆኑ በምርጫ ውጤት ላይም ተጽዕኖ የመፍጠረ አቅም እንዳላቸው ይገለጻል።
በሰሜናዊ ህንድ ከፍተኛ ምርት በማምረት የሚታወቁት የፑንጃብ እና ሀርያና ግዛት አርሶ አደሮች ትራክተር እየነዱ ወደ ዴልሂ ሲጓዙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ወጥተዋል።
ፖሊስ በአጥር ሽቦ፣ በሲሚንቶ ኮንክሪት እና በሌሎች ቁሶች አርሶ አደሮቹ ዘልቀው እንዳይገቡ የዴልሂ ከተማ ዳርቻ እየዘጋ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በዴልሂ ህዝባዊ ስብሰባ እንዳይካሄዱ ፖሊስ ክልከላ አስተላልፏል።
አርሶ አደሮቹ ለተቃውሞ የወጡት የማህበራት መሪዎች መንግስት እንዲደግፋቸው ወይም የአርሶ አደሮችን ገቢ በእጥፍ ለማሻደግ የገባውን ቃል እንዳተገብር ጫና እንዲደረግበት ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ነው ተብሏል።