ፖለቲካ
ህንዳውያን የአለማችን ግዙፉና ውዱ ምርጫ ድምጽ በመስጥ ላይ ይገኛሉ
969 ሚሊየን ሰዎች ለመምረጥ የተመዘገቡበት የ2024 የህንድ ጠቅላላ ምርጫ ለ42 ቀናት ይካሄዳል
በ1 ሚሊየን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን የሚሰጡ ህንዳውያን 543 የምክርቤት አባላትን ይመርጣሉ
ህንዳውያን የአለማችን ግዙፉና ውዱ ምርጫ በትናንትናው እለት የመጀመሪያ ዙር ድምጽ መስጥ መጀመራቸው ተነግሯል።
የህዝብ ብዛት መሪነትን ከቻይና የተረከበችው ህንድ በፈረንጆቹ ከትናንት ሚያዚያ 19 ሽከ ሰኔ 1 2024 ለስድስት ሳምንታት የሚዘልቅ የአለማችን ግዙፉን ምርጫ ማሄድ ጀምረዋል።
የህንድ ምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በጠቅላላ ምርጫው 969 ሚሊየን ሰዎች ድምጽ ለመስጠት ተመዝግበዋል፤ አሃዙ ከአውሮፓ ህዝብ የሚልቅ፤ ከአለም ህዝብም ከ10 በመቶ በላይ ነው።
ረጅም ጊዜ በሚወስደውና ፓርቲዎችም ለምርጫ ቅስቀሳና ለሌሎች ጉዳዮች ከፍተኛ ወጪ በሚያወጡበት ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባሃራቲያ ጃናፓ ፓርቲ (ቢጄፒ) እንደሚያሸንፍ ተገምቷል።
ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት የተሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአሁኑ ምርጫ ካሸነፉ ህንድን ለሶስተኛ ጊዜ የሚመሩ የሁለተኛው ሰዉ እንደሚሆኑም ነው የተገለጸው።
ስለአለማችን ውዱና ረጅሙ ምርጫ ቀጥሎ በቀረበው ስእላዊ መረጃ በዝርዝር ይመልከቱ፦