ኢንዶኔዥያ የብሪክስ ሙሉ አባል ሆና መቀላቀሏን ብራዚል አስታወቀች
በህዝብ ቁጥር ከአለም አራተኛ የሆነቸው ኢንዶኔዥያ ቡድኑን ለመቀላቀል ፍላጎታን ስትገልጽ ቆይታለች
የኢንዶኔዥያ አባልነት የጸደቀው ብሪክስ በ2023 በደቡብ አፍሪካ ባካሄደው ስብሰባ የአባል ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር በደረሰው ስምምነት መሰረት ነው ተብሏል
ኢንዶኔዥያ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗን የብራዚል መንግስት አስታውቋል።
ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት እያሳዩ ያሉት ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያና ደቡብ አፍሪካን ያካተተው ብሪክስ መስፋፋቱን ቀጥሏል።
የኢንዶኔዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ የብሪክስ አባልነት ከሌሎች በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር ስትራተጂካዊ ትብብር ለማድረግ ወሳኝ ነው ብሏል።
በህዝብ ቁጥር ከአለም አራተኛ የሆነቸው ኢንዶኔዥያ ቡድኑን ለመቀላቀል ፍላጎታን ስትገልጽ ቆይታለች።
የቡድኑ የ 2025 ፕሬዝደንት ብራዚል ባወጣችው መግለጫ አባል ሀገራት የኢንዶኔዥያን አባልነት በሙሉ ድምጽ ደግፈውታል ብላለች። የኢንዶኔዥያ አባልነት የጸደቀው ብሪክስ በ2023 በደቡብ አፍሪካ ባካሄደው ስብሰባ የአባል ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር በደረሰው ስምምነት መሰረት ነው ተብሏል።
ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ጃካርታ ቡድኑን ለመቀላቀል ፍቃድ ያገኘች ቢሆንም ባለፈው አመት ከተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በኋላ ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርባ ነበር። ፕሬዝደንት ፕራባዎ ሱቢያንቶ ባለፈው ጥቅምት ወር ስልጣን ይዘዋል።
"ኢንዶኔዥያ እንደሌሎች የቡድኑ አባል ሀገራት ሁሉ አለም አቀፉ የፋይናንስ ስርአት እንዲሻሻል ትፈልጋለች፤ በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ በሚገኙ ሀገራት መካከከል ጥልቅ ትብብር እንዲኖርም አስተዋጽኦ አድርጋለች" ብሏል የብራዚል መንግስት።
ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና አረብ ኢምሬትስም የእዚሁ ቡድን አባል ሆነዋል።