ሞስኮ በምስራቅ ዩክሬን ድል ሲቀናት፣ በምዕራብ ሩሲያ ደግሞ ውጊያው መጠንከሩ ተገለጸ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሩሲያ ኃይሎች ከፖክሮቭስክ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ 32 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የኩራክሆቭ ከተማ ተቆጣጥረዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሞስኮ በአምስት ወራት ውጊያ 15000 ወታደሮቿን በማጣት ከባድ ጉዳት ደርሶባታል ብለዋል
ሞስኮ በምስራቅ ዩክሬን ድል ሲቀናት፣ በምዕራብ ሩሲያ ደግሞ ውጊያው መጠንከሩ ተገለጸ።
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን እያካሄደች ባለው ጦርነት ድል መቀዳጀቷንና በምዕራብ ሩሲያ ደግሞ የዩክሬን ኃይሎች የከፈቱትን ጥቃት በመመከት ላይ መሆኗን በሁለት ቀናት በፊት አስታውቃለች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሩሲያ ኃይሎች ከፖክሮቭስክ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ 32 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የኩራክሆቭ ከተማ ተቆጣጥረዋል። የሩሲያ ኃይሎች በውጊያ ቀጠና ላለው የዩክሬን ጦር ሎጂስቲክ ለማመላለስ ወሳኝ የሆነችውን ፖክሮብስክን ለመያዝ ለበርካታ ወራት ጠንካራ ዘመቻ እያካሄዱ ናቸው።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሞስኮ በአምስት ወራት ውጊያ 15000 ወታደሮቿን በማጣት ከባድ ጉዳት ደርሶባታል ብለዋል። ዘለንስኪ ስለኩራክሆቭ ያሉት ነገር የለም።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው የዚች ከተማ መያዝ የሩሲያ ኃይሎች ወደ ዩክሬን ዶኔስክ ግዛት የሚያደርጉትን ፍጥነት ከፍ ያደርጋል። ሚኒስቴሩ አክሎም ከፖክሮቭስክ 8 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ዳቸንስኬ መንደርንም በቁጥጥር ስር ውላለች።
ዩክሬን ጦር የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ይዞታዎች ላይ 25 ጥቃቶች መሰንዘራቸውን ቢገልጹም ከተማዋ በሩሲያ እጁ ስለመውደቋ ያሉት ነገር የለም።
የዩክሬን የጦር ጸኃይዎች የዩክሬን ኃይሎች በሮኬት እና በግላይድ ቦምቦች ከባድ ጥቃት እየደረሰባቸው ተናግረዋል። ኩራክሆቭ በሩሲያ መግባት ግልጽ ነው ሲል ገልጿል።
ኦፕን ሶርስን በመጠቀም የግንባር ሁኔታዎችን የሚተነትነው ዲፕስቴት የተባለው የዩክሬን ቡድን አብዛኛው የኩራክሆቭ ከተማ ክፍል በሩሲያ ቁጥጥር ስር መግባቱን አሳይቷል።
ሁለቱም ተዋጊ ኃይሎች ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኃይት ከመግባታቸው በፊት በግንባር ያላቸውን ይዞታ ለማሻሻል ከፍተኛ ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ። ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ለዩክሬን እንደ ድል የሚቅጠረው በሩሲያ ክሩስክ ግዛት ውስጥ ቦታ መቆጣጠሯ ነው። ዩክሬን በኩርስክ ግዛት ውስጥ የያዘችው ቦታ ከሩሲያ ጋር ሊኖር በሚችል የሰላም ውይይት እንደመደራደሪያ ሊጠቅማት ይችላል ተብሏል።
ኪቭ ከሩሲያ ጋር ለድርድር የምትቀመጠው አሜሪካ የደህንነት ዋስተና የምትሰጣት ከሆነ ብቻ መሆኑን ዘለንስኪ ተናግረዋል። ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ትራምፕ ጦርነቱን ማስቆም የሚያስችል እቅድ እንደፈዳላቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል።