የተመራማሪዎቹን ፈጠራ ወደ ገበያ የሚቀርብበት መንገድ እየተፈለገ እንደሆነ ተገልጿል
የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ከሰውነታችን ሙቀት ላይ ቻርጅ ማድረግ የሚያስችለው ፈጠራ
የሰው ልጆችን ህይወት ቀላል በማድረግ የሚታወቀው ቴክኖሎጂ በየጊዜው እየዘመነ እና እየተሻሻለ ይገኛል፡፡
አሁን ደግሞ ከሰውነታችን ላይ በሚገኘው ሙቀት የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ፈጠራ ከጫፍ መድረሱን ተገልጿል፡፡
ዩሮ ኒውስ በቴክኖሎጂ አምዱ እንደዘገበው ከሆነ የእጅ ሰዓት እና መሰል በሰውነታችን ላይ የሚደረጉ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በቀላሉ ከሰውነታችን በሚያገኙት ሙቀት እንዲሰሩ ማድረግ የሚያስችል ፈጠራ ተሰርቷል፡፡
ፈጠራው በአውስትራሊያው ኩዊንስላንድ የቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ የተሰራ ሲሆን እስካሁን የእጅ ስልከ፣ የጆሮ ማዳመጫ፣ ቬንትሌተር እና መሰል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን እንዲሰሩ አድርገዋል፡፡
በዩንቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ቡድ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ወንዪ ቼን የፈጠራ ስራው በሰው ልጆች ሰውነት ውስጥ ያለውን ሙቀት ወደ ኤልክትሪክ ሀይልነት መቀየር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ይሁንና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ምርት ሂደት፣ የፈጠራ ዋጋ መናር አዲሱን ፈጠራ በቀላሉ ወደ ገበያ እንዳይወጣ አድርገውታል ሲሉም ፕሮፌሰር ወንዩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት ተመርተው እና አገልግሎት እየሰጡ ያሉት የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሙቀትን ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል መቀየር የሚያስችል ችፕስ ያላቸው ሲሆን አዲሱ ፈጠራ ግን ናኖ ባይንደርስ የተሰኘ ሀይል ሰጪ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡
ቴክኖሎጂው ከዚህ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ያላቸውን ሀይል ለረጅም ጊዜ እንዲጠሙ እና ሀይል እንዲቆጥቡ ተደርጎ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡