የተስፋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ውሳኔ ተላለፈ
በተመድ አባል ሀገራት ላይ በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በየዓመቱ ሐምሌ 5 ቀን የተስፋ ቀን ሆኖ እንዲከበር ወስነዋል

ኢትዮጵያ በዓሉን ደግፋ ድምጽ በሰጠችበት በዚህ ጉባኤ ላይ አሜሪካ ውሳኔውን ተቃውማለች
የተስፋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ውሳኔ ተላለፈ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው ውሳኔ የተስፋ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲበር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የረቂቅ ውሳኔ ሀሳቡን ኦስትሪያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሮኮ፣ ፊጂ እና ሌሎችም ሀገራት ያቀረቡ ሲሆን ዓለም አቀፍ የተስፋ ቀን በየዓመቱ በፈረንጆቹ ሐምሌ 12 እንዲከበር በአንላጫ ድምጽ ተሰጥቶበታል፡፡
የተመድ አባል ሀገራት የውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 166 ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ዕለቱ በ162 ሀገራት ድጋፍ ጸድቋል፡፡
በዚህ ውሳኔ ላይ አሜሪካ ሀሳቡን ተቃውማ ድምጽ የሰጠች ሲሆን ሕንድ ፣ ቱርክ፣ ፔሩ እና ፓራጓይ ደግሞ ድምጽ ተዓቅቦ ማድረጋቸውን ከተመድ ድረገጽ ላይ የወጣው ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ዓለም አቀፍ የተስፋ ቀን በየዓመቱ ስለ ተስፋ እና እኩልነት የተለያዩ ስራዎችን በመስራት እንደሚከበርም ተገልጿል፡፡
ውሳኔው መጽደቁን ተከትሎ ሁሉም የተመድ ተቋማት እና ድርጅቶች ስለ ተስፋ በተለያዩ መንገዶች ጉዳያቸው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ራሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተስፋን መሰረት በማድረግ መመስረቱን ምን ጊዜም ለሰዎች ተስፋን መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡