አሜሪካ “ዩክሬን የተወሰዱባት ግዛቶቿን ከሩሲያ የመመለስ ተስፋዋን ብትተው ይሻላል” አለች
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የዩክሬን የኔቶ አባልነት የማይሆን ነገር ነው ብለዋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/14/252-180919-whatsapp-image-2025-02-14-at-5.08.17-pm_700x400.jpeg)
ፑቲን የሰላም ስምምነት የሚኖረው ዩክሬን ኔቶን የመቀላቀል እቅዷን ከተወችና ሩሲያ ከያዘቻው ግዛቶች ጦሯን ካስወጣች ነው ብለዋል
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ዩክሬን በሩሲያ የተያዙባት ሁሉንም ግዛቶቿል ለማስመለስ ተስፋ ማድረግ እንድትተው አሳሰቡ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ፔት ሄግሰት ባሳለፍነው ረቡዕ እንደተናገሩት ዩክሬን የኔቶ አባልነት ጉዳይ የማይሆን ነገር ነው ብለዋል።
ዩክሬን በሩሲያ የተያዙባት ግዛቶችን ለማስመለስ ተስፋ ማድረግን በመተው በአንጻሩ ሰላምን ለማጣት ለሚደረግ ድርድር ብትዘጋጅ ይሻላል ሲሉም ምክር አዘል መልእክት አስተላፈዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ይህንን ካሉ ከሰዓታት በኋላም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ጦርት ማቆም በሚቻልበት ዙሪያ ድርድር ለማድረግ መስማማታውን በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጻቸው አስታውቀዋል።
በትራምፕ እና በሄግሴት የተሰጡት መግለጫዎች አንድ ላይ ሲደመር አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር በአውሮፓ እየተካሄደ ያለውን ግዙፉን የምድር ላይ ጦርነት በምን መልኩ ለማስቆም እንዳሰቡ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ፔት ሄግሰት ዩክሬን ኔቶ ለመግባት የምታደርገው ጥረት እንድትተውና የተያዙባትን ግዛቶች የመመለስ ተስፋዋን እንድታቆም የሰጡት ማስጠንቀቂያ አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር የሞስኮን እቅድ ለማሳካት የተቃረበ እንደሆነም ተነግሯል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ማንኛውም የሰላም ድርድርና ስምምነት የሚኖረው ዩክሬን ኔቶን የመቀላቀል እቅዷን ከተወችና ሩሲያ ከያዘቻው ግዛቶች ጦሯን ካስወጣች ነው ብለዋል።