ኢንተርፖል የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋዋ እንስት ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ
አንጎላዊቷ ኢዛቤል ዶስ ሳንቶስ ታስራ እንድትቀርብ ትዕዛዝ ወጥቶባታል ተብሏል
ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ያላት ኢዛቤል ሳንቶስ በስደት ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል
ኢንተርፖል የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋዋ እንስት ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ።
የቀድሞ የአንጎላ ፕሬዝዳንት ኤድዋርድ ዶስ ሳንቶስ ልጅ የሆነችው ኢዛቤል ዶስ ሳንቶስ የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋ እንደሆነች የፎርብስ ሪፖርት ያስረዳል።
አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ቅዛት ነጻ እንድትወጣ በማድረግ ለረጅም ዓመታት የሀገሪቱ መሪ በመሆን ካገለገሉ በኋላ በምርጫ ከስልጣን ተነስተዋል።
ስልጣን የተቆጣጣረው የወቅቱ የአንጎላ መንግስትም ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ቤተሰብ የሀገሪቱን ሀብት መዝብረዋል በሚል ክስ መስርቷል።
ይሄንን ተከትሎም ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ወይም ኢንተርፖል በአንጎላዊቷ የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋ እንስት ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኢዛቤል ዶስ ሳንቶስ በአሁን ወቅት ከአንጎላ ውጪ እንደሚኖሩ የተገለጸ ሲሆን በፖርቹጋል፣ ለንደን ወይም አረብ ኢምሬት ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል።
ኢዛቤል ዶስ ሳንቶስ ከዚህ በፊት ከአንጎላ መንግሥት ስለቀረበባቸው ክስ ከብዙሀን መገናኛዎች ለቀረበባባቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ "እኔ ምንም አይነት ሙስና አልፈጸምኩም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢንተርፖል ከወቅቱ የአንጎላ መንግስት በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በኢዛቤል ሳንቶስ ላይ የእስር ማዘዣ ሊያወጣ እንደቻለ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የ49 ዓመቷ ኢዛቤል አባቷ ኤድዋርዶ ሳንቶስ በፕሬዝዳንትነት ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ከባለቤታቸው ጋር በመሆን አንድ ቢሊዮን ዶላር ሙስና ፉጽመዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።