አለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክን ሊያራዝም በሚችልበት ሁኔታ መምከር ጀምሯል
የአለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ቶኪዮ 2020ን ሊያራዝም በሚችልበት ሁኔታ መምከር ጀምሯል
አለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የቶኪዮ 2020 የኦሎምፒክ ውድድርን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን እያየ ይገኛል፡፡
ኮሚቴው የተሰበሰበው እየተስፋፋ የመጣው ኮሮና ቫይረስ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ላይ ጥላ መጣሉን ተከትሎ ነው፡፡ ኮሚቴው ኮሮና ቫይረስ ሁለት አማራጮችን እንዲያስቀምጥ እንዳስገደደው አስታውቋል፡፡
ኦሎምፒኩ የሚጀመርበትን ሐምሌ 17ን ወደ ኋላ መጎተት ወይንም ወድድሩን በአንድ አመት ወይንም ከዚያ በላይ ወደፊት መግፋት ሲሆን መሰረዝ ግን ችግሩን እንደማይፈታና ማንንም እንደማይጠቅም ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ “ስለዚህ መሰረዝ አጀንዳ አይደለም”፤ ዝርዝር ውይይቶች በሚቀጥሉት አራት ሳምንታት ይካሄዳሉ ብሏል፡፡
የኮሚቴው ኦሎምፒኩን ለማስተላለፍ ማሰቡ በአለም አትሌቲክስ፣በአለምአቀፍ ፓራኦሎምፒክ ኮሚቴና በትላልቆቹ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች በበጎ ተወስዷል፡፡
ኮሚቴው በከፊልም ቢሆን ሀሳቡን ለመቀየር የወሰነው፣ ከአትሌቶች፣ከፌደሬሽኖችና ከብሄራዊ ኮሚቴዎች የመጣውን ጫና ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የቶኪዮ ኦሎምፒክ አዘጋጆች ግን ወድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ እየወተወቱ ይገኛሉ፡፡