የሊቢያ የአንድነት መንግስት ሃላፊ ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ አሉ
ሊቢያ ኮሎኔል ጋዳፊ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ለአስርት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ ብጥብጥ ውስጥ ቆይታለች
ሁለቱ የሊቢያ ተቀናቃኞች በሞሮኮ ከተገናኙ በኋላ ሊቢያ የአንድነት መንግስት ሃላፊው ስልጣን እንደሚለቁ ገለጹ
ሁለቱ የሊቢያ ተቀናቃኞች በሞሮኮ ከተገናኙ በኋላ ሊቢያ የአንድነት መንግስት ሃላፊው ስልጣን እንደሚለቁ ገለጹ
በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያለው የሊቢያ ብሄራዊ ስምምነት መንግስት የሰላም ስምምነቱን ለማስኬድ ሲባል በ6 ሳምንታት ውስጥ ስልጣን እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 በሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት/ኔቶ አጋዥነት ሊቢያን ለረጅም ጊዜ የመሩት ኮሎኔል ጋዳፊ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ለአስርት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ ብጥብጥ ውስጥ ቆይታለች፡፡
የብሄራዊ ስምምነት መንግስቱ መሪ ፋይዝ አል ሲራጅ በምስራቃዊ ሊቢያ በተቀናቃኛቸው ከሊፋ ሃፍታር ከሚመራው ጦር ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገብተው ብዙዎችን ለሞትና ለስደት ዳርገዋል፡፡
ባለፈው ወር ሁለቱ ኃይሎች ለሰላም ስምምት ሞሮኮ በመገናኘት ድንገተኛ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው፣ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብተው ነበር፡፡
ሲራጅ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልእክት በድርድሩ ሂደት በሚደረሰው ውሳኔ የሚወሰን ቢሆንም ስልጣን ለመልቀቅ ኃሳብ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ኃላፊነቴን ከመጭው ጥቅምት ወር በፊት ስልጣኑን ለሚቀጥለው አስተዳደር አስረክባለሁ ብለዋል፡፡
በሞሮኮ እየተካሄደ ያለውን የመጀመሪያ ድርድርም መቀበላቸውን አሳውቀዋል፡፡ የሊቢያ ዲያሎግ የተባለው የሞሮኮ ጉባኤ ከብሄራዊ የስምምነት መንግስቱ አምስታ አባላት እንዲሁም ዋና ከተማውን በምስራዊቷ ቱብሩክ ካደረገው ተቃናቃኝ አምስት ተወካዮችን አገናኝቷል፡፡
ድርድሩ ትኩረቱን ያደረገው የሀገሪቱ ከፍተኛ ተቋማት ሹመት ላይ ሲሆን በዚህም የሊቢያ ማእከላዊ ባንክ፣የብሄራዊ ባንክ ኮርፖሬሽንና የጦር ሃይሎች ባለስልጣናትን ማን ይምራው የሚለውን ላይ ሲሆን የተቋማቱ መሪዎች ስምም ተጠቅሷል፡፡