ከተመላሽ ስደተኞቹ ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው አይኦኤም ገልጿል
ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ62 ሺህ በላይ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መቀበሉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(አይኦኤም) አስታወቀ።
ድርጅቱ ለአል ዐይን እንዳስታወቀው ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ወደተለያዩ ሀገራት የተሰደዱ ከ62 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ተመላሽ ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገዱን ገልጿል።
ሱዳን፤ ሳውዲ አረቢያ ፤ሶማሊያ፤ ጅቡቲ እና ኬንያ ከ10 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የተመለሱባቸው ሀገራት ናቸው።
በየዕለቱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከመካከለኛው ምስራቅ እና ጎረቤት ሀገራት በመመለስ ላይ ሲሆኑ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ ከ3 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ተብሏል።
ተመላሽ ስደተኞቹ በአዲስ አበባ፤ድሬዳዋ፤ ጅግጅጋ፤ ቦረና፤ጌድዮ፤ምዕራብ ወለጋና ትግራይ እና አማራ ክልል በሚገኙ ጣቢያዎች መሰረታዊ የጤና እና ምገብ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም ድርጅቱ ገልጿል።
ከተመላሽ ስደተኞቹ ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ጾታዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሲሆኑ የስነ ልቦና ህክምና እንደተደረገላቸው ተገልጿል፡፡