ፖለቲካ
ኢራን በጋዝ ቱቦዎቿ ላይ ለደረሰው ፍንዳታ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች
ከደቡብ ወደ ሰሜን የተዘረጉ ሁለት የጋዝ ቱቦዎች በሁለት ፍንዳታዎች ተመትተዋል።
እስራኤል ባለፈው ሳምንት ከደረሰው የጋዝ ቱቦዎች ፍንዳታ ጀርባ እንዳለች የኢራን የነዳጅ ሚኒስቴር ጃቫል ኦውጂ ተናግረዋል
ኢራን በጋዝ ማመላለሻ ቱቦዎቿ ላይ ጥቃት እንዲደርስ እስራኤል አሲራለች ሰትል ከሰሰች።
እስራኤል ባለፈው ሳምንት ከሰሜን ወደ ደቡብ በተዘረጉ የጋዝ ቱቦዎች ላይ ከደረሰው ፍንዳታ ጀርባ እንዳለች የኢራን የነዳጅ ሚኒስቴር ጃቫል ኦውጂ ተናግረዋል።
ኦውጂ ፍንዳታው በተከሰሱበት ወቅት ጥቃቱን "በሽብርተኞች የተቀነባበረ ነው" ብለው ነበር።
ሚኒስትሩ "ጠላት የጋዝ አቅርቦት ስርጭት ለማወክ ሞክሮ ነበር። ነገርግን ሰራተኞቻችን በጥቂት ሰአታት ልዩነት የተጎዳውን መጠገናቸውን " ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል ኢራን ባቀረበችው ክስ ላይ ምላሽ አልሰጠችም ተብሏል።
ኢራን ባለፈው ታህሳሳ ወር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያለው የመረጃ ጠላፊ ቡድን 70 በመቶ የሚሆነውን የፔትሮል ጣቢያዎች ስራ አስተጓጉሏል የሚል ክስ አቅርባ ነበር።
በአሁኑ ወቅት ከሀማስ ጋር እየተዋጋች ያለችው እስራኤል፣ ኢራን ከሀማስ ጋር ለተሰለፉት የሊባኖሱን ሂዝቦላ እና የየመኑን ሀውቲ አማጺ በመደገፍ ትከሳታለች።
የእስራኤል ዋነኛ አጋር የሆነችው አሜሪካም በቀይ ባህር ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ያሉትን የሀውቲ አማጺያንን በመደገፍ ኢራንን ከሳለች።