ባይደን በጉብኝታቸው ወቅት ኢራን ኒውከሌር እንዳይኖራት መስራት የሚለው ጉዳይ አንደኛው አጀንዳ ነበር
ኢራን አሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ወቅት ውጥረት ለመፍጠር የኢራን ፍራቻን ወይም ኢራኖፎቢያን ተጠቅማች ስትል ከሳለች፡፡
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እሁድ እለት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ወቅት ያቀረቡትን ተከታታይ ውንጀላዎች ውድቅ ማድረጉን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ኢራን አሜሪካ "ኢራኖፎቢያ"ን ቀጣናዊ ውጥረት ለመፍጠር ተጠቅማለች የሚል ክስ አቅርባለች፡፡
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ የባይደን ጉብኝት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ "አሜሪካ በድጋሚ በቀጠናው ውጥረት እና ቀውስ ለመፍጠር ፈልጋለች"፡፡
ባይደን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ባደረጉት ጉብኝት ኢራን በተግባሯ ቀጣናውን እንዳይረጋጋ እያደረገች ነው የሚል ክስ ሰንዝረዋል፤ አሜሪካ "ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታገኝ" እንደሚያደርጉ፣ ተናግረዋል፡፡
በመግለጫው ላይ ካናኒ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መግለጫ መሠረተ ቢስ እና በቀጠናው ውስጥ ውጥረቶችን ከማስነሳት እና ከመፍጠር ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ነው ብለዋል ።
ቃል አቀባዩ አሜሪካ በክልሉ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ በምታደርገው ተከታታይ ጣልቃ ገብነት፣ ተደጋጋሚ ወታደራዊ ወረራ እና ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በቀጣናው ውጥረት እና ቀውስ ለመፍጠር እየሞከረች ነው በማለት አውግዘዋል።
በመግለጫው ባለፉት አስርት አመታት የፍልስጤምን ህዝብ መብት ሲጣስ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን “ጭፍን እና ያልተገደበ ድጋፍ” አውግዘዋል።
ካናኒ እንደተናገሩት ኢራን የኒውክሌር ቴክኖሎጅን አለምአቀፍ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደምትጠቀም እና ማእቀቡ እንዲነሳ እንደምትጥር ገልጸዋል፡፡
ወደ ኒውክሌር መርሃ ግብሩ ስንመጣ ካናኒ የኢራንን የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በሰላማዊ መንገድ የመጠቀም ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ በአለምአቀፍ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ደግሟል እና ኢራን ማዕቀቡን ለማንሳት ድርድርዋን እንደምትቀጥል ተናግሯል።
ኢራን ለአካባቢው ፀጥታ፣ ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት ገንቢ ጥረቶችን ለማቅረብ ከአካባቢው ጎረቤቶች ጋር የሚደረገውን ውይይት እና ትብብር እንደምትቀበል በመግለጫው ተጠቅሷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሰሞኑ እስራኤል እና ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ባይደን በጉብኝታቸው ወቅት ኢራን ኒውከሌር እንዳይኖራት መስራት የሚለው ጉዳይ አንደኛው አጀንዳ ነበር፡፡