አሜሪካ እና እስራኤል፤ ኢራን የኒውክሌር መሳሪያ እንዳትታጠቅ ለማድረግ የቃል ኪዳን ስምምነት ሊፈራረሙ ነው
ፕሬዝዳንት ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ላፒድ ጋር ተወያይተዋል
አሜሪካ ስምምነቱ በአሜሪካና እና በእስራኤል መካከል የቆየውን የጸጥታ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጻለች
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉትን ጉብኝት በእስራኤል ጀምረዋል፡፡
በትናንትናው እለት ፕሬዝደንት ባይደን በእስራኤል ዴቪድ ቦንጎሪዎን አየር ማረፊያ ሲደርሱ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሌሎች ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ያየር ላፒድ በባይደን የመካከለኛው ምስራቅ ጉዞ በሁለተኛው ቀን ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታገኝ ለመከላከል ቃል የገቡትን የጋራ ስምምነት በዛሬው እለተ ይፈራረማሉ።
ከፍተኛ የሆኑ የባይደን አስተዳደር ባለስልጣን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ስምምነቱ በአሜሪካና እና በእስራኤል መካከል የቆየውን የጸጥታ ግንኙነት የበለጠ ያሰፋል፡፡
ባለሥልጣኑ "ይህ መግለጫ በጣም ጠቃሚ ነው፤ እና ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንድታገኝ በፍጹም ላለመፍቀድ እና የኢራንን የማተራመስ ተግባራት በተለይም የእስራኤልን ስጋት ለመፍታት ቁርጠኝነትን ያካትታል" ብለዋል ።
ባይደን በፈረንጆቹ በ2021 መጀመሪያ ላይ ስልጣኑን ከተረከቡ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዞ በትናንትናው እለት እስራኤል ገብተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ላፒድ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን ጉብኝታቸውን ዛሬ በእስራኤል የሚጀምሩ ሲሆን፤ በመቀጠልም ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያቀኑ ይሆናል።
ባይደን በእስራኤል የሚኖራቸውን ቆይታ ሲያገባድዱ ከሳዑዲ አረቢያ እና በባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ከሚገኙ የግብጽ፣ ኢራቅ እና ዮርዳኖስ መሪዎች ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏዋል፡፡