እስራኤል በአለም ላይ የእጅግ ዘመናዊ የአየር ሃይል ባለቤት ነች
ኢራን በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ ከወሰደች በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት በእጅጉ እያለ መጥቷል።
ኢራን የቅዳሜ ሌሊቲን ጥቃት የሰነዘረችው እስራኤል ከ2 ሳምንት በፊት በሶሪያ ደማስቆ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላይ ለፈጸመቸው ጥታቅ መልስ መሆኑንመ አሰታውቃለች።
ይህንን ተከትሎም በሁለቱ ሀገራ መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት በእጅጉ እየተካረረ የመጣ ሲሆን፤ የዓለም ሀገራት በበኩላቸው ሀገራቱ ወደ ግጭት ከሚያስገቡ ተግባራት እንዲቆጠቡ እያሳሰቡ ነው።
ወታራዊ ፍጥጫ ውስጥ የገቡት የኢራን እና የእስራኤል ወታደራዊ ጥንካሬ በንጽጽር ምን ይመስላል?
ኢራን በጂኦግራፊካል አቀማመጥም ከእስራኤል የምትበልጥ ሲሆን፤ በህዝብ ብዛትም ቢሆን 90 ሚሊየን ገደማ ህዝብ ያላት ኢራን ከእስራኤል በ10 እጥፍ ትበልጣለች። ነገር ግን ይህ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይልን አይወክልም።
ኢራን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚሳዔሎች እና ድሮኖች ልማት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ኢንቨስት ስታደርግ የቆየች ሲሆን፤ ከራሷ አልፎም ለየመኑ ሃውቲ እና ለሊባሱ ሄዝቦላም ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን ታቀርባለች።
ኢራን የሚጎድላት ነገር ቢኖር ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርዓት እና ተዋጊ ጄቶች ሲሆኑ፤ ይህንን ለማሻሻል ኢራን ከሩሲያ ጋር በትብብር እየሰራች እንደሆነም ይነገራል።
ከዚህ ጋር ሲነጻጸር እስራኤል በዓለም ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የአየር ኃይል ካላቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን፤ እንደ ኢይአይኤስ ወታደራዊ መረጃ ከሆነ እስራኤል F15፣ F16 እና የቅርብ ምርት የሆነውን ኤፍ-35 ስውር ጄቶችን ጨምሮ ቢያንስ 14 ስኳድሮን ጄቶች አሏት።
ኢራን እና እስራኤል አቅም በንጽጽር እንደሚከተለው ቀርቧል፤
አጠቃላይ የህዝብ ብዛት
ኢራን፤ 87.6 ሚሊየን
እስራኤል፤ 9.04 ሚሊየን
ለወታደራዊ አገልግሎት ብቁ የሆኑ
ኢራን፤ 41.17 ሚሊየን
እስራኤል፤ 3.16 ሚሊየን
ያላቸው የሰራዊት መጠን
በወታርነት እያገለገሉ ያሉ
ኢራን፤ 610 ሺህ
እስራኤል፤ 170 ሺህ
ተጠባባቂ ኃይል
ኢራን፤ 350 ሺህ
እስራኤል፤ 465 ሺህ
ወታደራዊ በጀት
ኢራን፤ 9.95 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር
እስራኤል፤: 24.4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር
የአየር ኃይል ጥንካሬ
አጠቃላይ የውጊያ አውሮፕላኖች
ኢራን ፤ 186
እስራኤል፤ 241
የውጊያ ሄሊኮፕተር ባዛት
ኢራን፤ 13
እስራኤል፤ 48
የምድር ኃይል
የታንኮች ብዛት
ኢራን፤ 1 ሺህ 996
እስራኤል፤ 1 ሺህ 370
ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች
ኢራን 65 ሺህ 765
እስራኤል 43 ሺህ 407
የባህር ኃይል
የጦር መርከቦች ብዛት
ኢራን፤ 101
እስራኤል፤ 67
የባሀር ሰርጓጅ መርከብ
ኢራን፤ 19
እስራኤል፤ 5