ኢራን በእስራኤል ላይ የፈጸመችው ጥቃት ምን ያክል ጉዳት አድርሷል?
እስራኤል ከተተኮሱባት ከ300 በላይ ድሮኖና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን አከሽፊያለሁ ብላለች
ኢራን በካህይበር ሚሳዔል ወሳኝ የሆነ የእስራኤል የአየር ኃይል ጣቢያን መምታቷን አስታውቃለች
ኢራን ሌሊቱን በጀመረችው ቀጥተኛ ጥቃት ወደ እስራኤል በርካታ ቁጥር ያላቸው ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን መተኮሷን አስታውቃለች።
እስራኤል ባሳለፍነው ሳምንት በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኝ የኢራን ኤምባሲ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ዘጠኝ ኢራናዊያ መገደላቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ በኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን እንደምትበቀል ስትዝት የቆየችው ኢራን በዛሬው እለት መጠነ ሰፊ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃተ ወደ ቴልአቪቭ መክፈቷን አስታውቃለች።
እስራኤል እንደስታወቀችው ከ300 በላይ ድሮኖች አና ሚሳዔሎች ከኢራን፣ የመን እና ኢራቅ ውስጥ ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል።
ኢራን ጥቃትና ያስከተለው ጉዳት
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አድሚራል ዳንኤል ሀግሪ፤ ወደ እስራኤል ከተተኮሱ ከ300 በላይ ድሮኖና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን ማክሸፍ እንደተቻለ ተናግረዋል።
በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ እና ፈረንሳይ እርዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢራን ድሮኖችና ሚዔሎች ድንበር ላይ ተመትተው ወድቀዋል።
እስራኤል ተከላከልኩ ትበል እንጂ የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤል አየር መከላከያዎችን ጥሰው በመግባት በርካታ ኢላማዎችን መምታታቸው መረጃዎች እየወጡ ነው።
ኢራን ካህይበር የተባለው አደገኛው ሚሳዔል ወሳኝ የሆነ የእስራኤል የአየር ኃይል ጣቢያን መምታቱን የኢራን ዜና አገልግሎት አስታውቋል።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል በኤክስ ገጽ (በቀድሞ ትዊተር ገጽ) ባወጣው መረጃ አነስተኛ ቁጥር ላቸው ቦታዎች መመታታቸውን እና በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸው ጉዳቶች መድረሳቸውን አረጋግጠቷል።
አነስተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ በደቡባዊ እስራኤል የሚገኝ የእስራኤል ጦር መዛዣ ጣቢያ እንደሚገኝበትም የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቋል።
ስለ ጥቃቱ የተሰጡ አስተያየቶች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ሀገራው ከኢራን የሚሰነዘርባትን ማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ እንደምትቀም ገልጸው፤ “እኛን የጎዳ ሁሉ ይጎዳል” ሲሉ ዝተዋል።
የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ከህሚኒ በሰጡት አስተያየት “ጺዮናዊው አስተዳደር ይቀጣል” ሲሉ የዛቱ ሲሆን፤ በተመድ የኢራን ተወካይ በበኩላቸው አሜሪካ በዚህ ጉዳይ ጣልቃ እንዳትገባ አስተንቅቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ “አሜሪካ በእስራኤል ላይ ያላት ፖሊሲ እንደ ብረት የጠነከረ ነው” ያሉ ሲሆን፤ የብሪታያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሱናክ እና የጀርመኑ መራሄ መንግስት ስቾልዝ የባይደንንን ሀሳብ ደግፈው መግለጫ ሰጥተዋል።