ሀይፐር ሶኒክ ባልስቲክ ሚሳይሉ በኢራን የእስልምና አብዮተኞች ጥበቃ እንደተሰራ ተገልጿል
ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ ሀይፐር ሶኒክ ሚሳይል መስራቷን ገለጸች፡፡
የመካከለኛዋ ምስራቅ ኢራን ሀይፐር ሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳይል መገንባቷን የገለጸች ሲሆን ሚሳኤሉ በኢራን የአብዮተኞች ጥበቃ እንደተሰራ ተገልጿል፡፡
ኢራን ኑክሌር አረር እንዳትታጠቅ ተደጋጋሚ ማዕቀቦች በአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የተጣለባት ሲሆን እገዳውን ለማስነሳት በፈረንጆቹ 2015 ላይ በኦስትሪያ ቬና ከተማ ስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
ይሁንና የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ሲመጡ ይሄንን ስምምነት መሰረዛቸውን ተከትሎ በኢራን እና ምዕራባዊያን መካከል ግንኙነቱ ዳግም ሊሻክር ችሏል፡፡
ኢራንም የኑክሌር ማብላላቷን የቀጠለች ሲሆን የሀገሪቱ ጦር ዘመናዊ ሀይፐር ሶኒክ ባልስቲክ ሚሳኤል ሰርቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በእስላሚክ አብዮተኞች ጥበቃ ኮርፖሬሽን የኤሮ ስፔስ ሀላፊ ጀነራል አሚር አሊ በሚሳኤሉ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ እንዳሉት አዲሱ ሚሳኤል ፍጥነቱ ለእይታ አስቸጋሪ እና ከድምጽም በላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአየር ላይ የሚደርሱ ማናቸውንም ጥቃቶች መፈጸም ያስችላል የተባለለት ይህ ሚሳኤል በኢራን የትውልድ ታሪክ አዲስ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኢራን የኢራን የሚሳኤል ፕሮግራም ጠንሳሽ እና አባት በመባል የሚታወቁት ሀሰን ቴህራኒ የተገደለበትን 11ኛ ዓመት በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡
ኢራን በአሜሪካ ተደጋጋሚ ማዕቀቦች ቢጣልባትም ሚሳኤል ሰርታ መታጠቅ መቻሏን የተናገሩት ጀነራል አሚር አሊ ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤሉ ከኢራን የ1979 አቢዮት በኋላ የጠሰራ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ከድምጽ አምስት እጥፍ ፍጥነት እንዳለው የተገለጸው ይህ ሀየፐር ሶኒክ ሚሳኤል በሰው ልጅ መደበኛ እይታ ውስጥ መለየት እንደማይቻል እና መትቶ መጣል የማይቻል እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ጀነራል አሚር አክለውም ኢራን የኢኮኖሚ፣የጸጥታ እና የፖለቲካ ጦርነት ውስጥ መሆኗን ጠቅሰው አዲሱ ሚሳኤል በዜጎቻች