የኢራን ፕሬዝዳንት አሜሪካ በኢራን ላይ “የአረቦች ህዝባዊ አመጽ” ለመድገም ያደረገችው ሙከራ ከሽፏል አሉ
የ22 ዓመቷ ኢራናዊት ኩርድ ማህሳ አሚኒ ሞት በኢራን ታይቶ የማይታወቅ የተቃውሞ ማዕበል ቀስቅሷል
ፕሬዝዳንት ራይሲ፤ በርካታ የሀገሪቱ ግዛቶችና ከተሞች ፍጹም በሆነ መረጋጋት ላይ ናቸው ብለዋል
የ22 ዓመቷ ኢራናዊት ኩርድ ማህሳ ጸጉርሽን ያልተገባ አለባበስ ለብሰሻል በሚል በቴህራን የደንብ አስከባሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ከዋለች ከሶስት ቀናት በኋላ በእስር ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉ የሚታወስ ነው።
የማህሳ አሚኒ ሞት ታዲያ በኢራን ታይቶ የማይታወቅ የተቃውሞ ማዕበል ቀስቅሷል፡፡
ተቀውሞው እንደፈረንጆቹ በ1979 በአሜሪካ የሚደገፈውን ሻህ ከስልጣን ለማስወገድ ከተደረገው የእስልምና አብዮት ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች (አብዛኛዎቹ እና አክቲቪስቶች) የሞቱበትም ሆነዋል፡፡
ይህም በኢራን ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ተደረገው የሚታዩት አያቶላ አሊ ካሜኒ እንደዚህ አይነት ተቃውሞ ሲገጥማቸው የመጀመሪያው መሆኑም ጭምር ይገለጻል፡፡
በሁኔታው የተደናገጡት የቴህራን ባለስልጣናት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከሳምንታት በፊት ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ሽፋን በማድረግ ቴህራንን “የማተራመስ ፖሊሲ” እየተገበረች ነው መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ራይሲ"የኢራን በውስጥ ጥንካሬዋ ላይ የተመሰረተ እድገት ማስመዝገብ ኃያላኖቹ ድንጋጤ ፈጥሮባቿል " ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የኢራን መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ በበኩላቸው የእስላማዊ ሪፐብሊክ ቀንደኛ ጠላቶች አሜሪካና እና እስራኤል “ሁከትና ብጥብጥ” እንዲቀሰቀስ አድርገዋል ሲሉ መክሰሳቸው ይታወሳል።
"ዛሬ፤ ሁሉም ሰው በእነዚህ የጎዳና ላይ ረብሻዎች ውስጥ የጠላቶችን ተሳትፎ መኖሩ ያረጋግጣል"ም ነበር ያሉት አያቶላ አሊ ካሜኒ።
ይሁን እንጅ የአሜሪካ ሴራ ሊሳካ እንዳመይችልና እንደከሸፈ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ መናገራቸው ኤኤፍፒ የኢራን ሚዲያ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ኢብራሂም ራይሲ “እንደፈረንጆቹ በ2011 በኢስላሚክ ሪፐብሊክ የተካሄደውን የአረቦች ህዝባዊ አመጽ ለመድገም አሜሪካ ያደረገችውን ሙከራ ከሽፏል” ብለዋል፡፡
ፐሬዝዳንቱ አሁን ላይ በበርካታ የሀገሪቱ ግዛቶችና ከተሞች ፍጹም የሆነ መረጋጋት እንዳለም ተናግረዋል፡፡
የኢራንን ክስ ውድቅ የምታደርገው አሜሪካ በበኩሏ የኢራን ክስ ውድቅ ደረገች ሲሆን፤ ቴህራን ሰላማዊ ሰልፎችን ለማፈን የሄደችበት ርቅት አውግዛለች፡፡ተቃውሞ “አፍነዋል”ባለቻቸው በሰባት የኢራን ባለስልጣናት ላይም ማዕቀብ ጥላለች፡፡