የዓለም ጤና ድርጅት በኢራን በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ሞት እና ጉዳት አስጨንቆኛል አለ
የ22 አመቷ ማህሳ አሚኒ ህልፈት ተክተሎ በኢራን ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱ የሚታወቅ ነው
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተቃዋሚዎች ላይ በተወሰደው እርምጃ ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል
በኢራን ውስጥ በተቃዋሚዎች እና በሌሎች ሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ሞት እና መቁሰል በጣም እንዳስጨነቃቸው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገለጹ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ፤ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ ያልተገደበ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉ በጣም አስፈላጊ መሆኑም ተናገርዋል፡፡
ማህሳ አሚኒ የተባለች የ22 አመቷ የኩርድ ሴት ተገቢ ያልሆነ አለባበስ ለብሳለች በሚለ በፖሊስ ከተያዘች በኋላ በፖሊስ ቁጥጥር ስል ሳለች ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ ነው በኢራን ትልቅ ተቃውሞና ብጥብጥ መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡
ተቃውሞው ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት የሀገሪቱ መንግስት ፓሊሶች እና ሚሊሺያ ሃይሎችን በማሰማራት በሀገሪቱ የኩርድ አካባቢዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉም የሮይተስር ዘገባ ያመለክታል፡፡
በዚህም ተቃውሞውን የተቀላቀሉ በርካታ ልጃገረዶች ሞሞታቸው እንዲሁም በመቶውች የሚቆጠሩ ለእስር መዳረጋቸው እየተገለጸ ነው፡፡
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተቃውሞ ሰልፎች ላይ በተወሰደው እርምጃ ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋይት ሃውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ዣን ፒየር ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ ዋሽንግተን "ሞስኮ ተቃዋሚዎችን በመጨፍለቅ ረገድ ያላትን ሰፊ ልምድ በመጠቀም ለኢራን ምክር ትሰጣለች ብላ ታምናለች” እናም ይህ ጉዳይ ያሳስበናል ማለታቸው ይታወሳል።
የዋይት ሀውስ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ በበኩላቸው “ተቃዋሚዎችን ለመጨፍለቅ በሚደረግ ጥረት የሚታዩ ጸጥታ ኃይሎች ድርጊቶች እያጤንን ነው እናም በሚያሳዝን ሁኔታ ሩሲያ መሰል ልምድ እንዳለት ተረድተናል" ማለታቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል።
አሜሪካ በኢራን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በተቃዋሚዎች ላይ ለሚወሰዱ እርምጃዎች ሞስንኮ ብትከስም የቴህራን ባለስልጣናት ግን ከጅምሩም ቢሆን ሀገሪቱ በተቃውሞ ሰልፎች እንድትናጥ ያደረገችው አሜሪካ ናት የሚል ክስ ሲያቀርቡ ተደምጠዋል።
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ አሜሪካ በሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ሽፋን በማድረግ ቴህራንን “የማተራመስ ፖሊሲ” እየተገበረች ነው ሲሉ በቅርቡ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ራይሲ"የኢራን በውስጥ ጥንካሬዋ ላይ የተመሰረተ እድገት ማስመዝገብ ኃያላኖቹ ድንጋጤ ፈጥሮባቿል " ሲሉ ተናግረዋል።
ኢራን መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ በበኩላቸው የእስላማዊ ሪፐብሊክ ቀንደኛ ጠላቶች አሜሪካና እና እስራኤል “ሁከትና ብጥብጥ” እንዲቀሰቀስ አድርገዋል ሲሉም ከሰዋል።
"ዛሬ፤ ሁሉም ሰው በእነዚህ የጎዳና ላይ ረብሻዎች ውስጥ የጠላቶችን ተሳትፎ መኖሩ ያረጋግጣል"ም ነበር ያሉት አያቶላ አሊ ካሜኒ።
"እንደ ፕሮፓጋንዳ፣ በአእምሮ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር፣ ደስታን መፍጠር፣ ማበረታታት አልፎ ተርፎም ተቀጣጣይ ቁሶችን ማምረትን የመሳሰሉ የጠላት ድርጊቶች አሁን ሙሉ በሙሉ ግልጽ ሆነዋል" ሲሉም አክለዋል።