ኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ለሩሲያ መላኳ ተገለጸ
በተመድ የኢራን ቋሚ ተወካይ ባወጣው መግለጫ ኢራን በወታራዊ ትብብር ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ከሩሲያ የረጅም ጊዜ ግንኙነት አላት ብሏል
በደርዘን የሚቆጠሩ የሩሲያ ወታደሮች ፋዝ-360 የተባለውን የኢራን መሳሪያ ለመጠቀም ኢራን ውስጥ በስልጠና ላይ ናቸው ተብሏል
ኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለስቲክ ሚሳይሎችን ለሩሲያ መላኳ ተገለጸ።
በደርዘን የሚቆጠሩ የሩሲያ ወታደሮች ፋዝ-360 የተባለውን የኢራን መሳሪያ ለመጠቀም ኢራን ውስጥ በስልጠና ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ኢራን በሳተላይት የሚመሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳይሎችን ሩሲያ ማቀበሏ የማይቀር ነው።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒሰትር ተወካዮች ባለፈው ታህሳስ ወር አባቢል በተባለው የኢራኑ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ኦርጋናይዜሽን(ኤአይኦ) የተገነቡ ፋዝ-360 እና ሌሎች ባለስቲክ ሚሳይሎችን ለመረከብ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ውል መግባታቸውን ዘገባው የደህነት ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
150 ኪሎ የሚመዝን ተተኳሽ ያለው 120 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል ሚሳይል ማስወንጨፍ የሚችለውን ፋዝ-360 አጠቃቀም ለማወቅ የሩሲያ ወታደሮች ወደ ኢራን መሄዳቸውም ተገልጿል። ሞስኮ የራሷ በርካታ ባለስቲክ ሚሳይሎች ያሏት ቢሆንም የኢራኖቹን ለአጭር ርቀት፣ የራሷን ደግሞ ከግንባር በረጅም ርቀት የሚገኙ ኢላማዎቸን ለመምታት እንደምትፈልግ ወታደራዊ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ምክርቤት ቤት ቃል አቀባይ ኢራን ለሩሲያ የጦር መሳሪያ የምትሰጥ ከሆነ ከሜሪካ እና የኔቶ አጋሮቿ እንዲሁም የቡድን ሰባት ሀገራት ቡድን "ፈጣን እና ጥብቅ እርምጃ" ለመውሰድ ተዘጋጅቿል ብለዋል።
ቃል አቀባዩ እዳሉት ኢራን ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ወረራ ድጋፍ የምሰጥ ከሆነ ያልተጠበቀ መካከረር ያስከትላል ብለዋል።
"ሩሲያ በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት ካወጀች ጀምሮ ኃይት ሀውስ በኢራን እና በሩሲያ መካከል ያለው እየጠነከረ የመጣው ግንኘነት እንደሚያሳስበው አስጠንቅቋል።"
በተመድ የኢራን ቋሚ ተወካይ ባወጣው መግለጫ ኢራን በወታራዊ ትብብር ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ከሩሲያ የረጅም ጊዜ ግንኙነት አላት ብሏል።
"ያም ሆኖ ከስነምግባር አኳያ ኢራን በዩክሬን ጦርነት ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሚሳይሎችን ጨምሮ የጦር መሳሪያዎች አስተላልፋ አትሰጥም" ሲል አክሏል መግለጫው።
ለዩክሬን የገንዘብ የጦር መሳሪያ ድጋፍ የሚያደርጉት ምዕራባውያን ሀገራት፣ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እያቀረቡ ነው የሚል ክስ ያቀርባሉ። ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ግን ይህን ክስ አይቀበሉትም።